የ180 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት ትብብር እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የ180 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ የያዘውን የ2023-2025 የኢትዮጵያ እና የጣልያን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የፋይናንስ ስምምነቱ በኢኮኖሚ ልማት በተለይ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች እና በጤና እና በትምህርት መሠረታዊ አገልግሎት አቅርቦት፣ ቁልፍ በሆኑ ተግባራት ላይ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም እና የአሥር ዓመት የልማት ዕቅዳችንን ለማስቀጠል የሚደግፍ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ሁለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነትን መግለጻቸውም ተመላክቷል፡፡ FBC

See also  ታዳጊ ሀገራት ከሩሲያ ማዳበሪያ እንዳይሸምቱ የአውሮፓ ህብረት ፕሮፖዛል

Leave a Reply