BRICS አዳዲስ አባል ሀገራትን በይፋ መቀበሉን አስታወቀ፤ ውሳኔው ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ውጤት ነው ተብሏል

ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሲያስታውቁ፣ ጎን ለጎን ዜናው ሃሰት ነው በሚል ዜጎችን ለማውናበድ ተጠምደው ለነበሩ ራሱ ብሪክስ መልስ የሚሆን ማረጋገጫ ሰጥቷል። ኤሌያስ መሰረት የሚመራው የፌስ ቡክ ገጽ ዜናውን “ሃሰት በማለት” ለማውገዝና ለማጣታል ቅድሚያ ሚና የተጫወተ እንደሆነ ተከታዮቹ ካሰረጩት መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

ዜናው ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ያስደሰተ፣ በጉጉት ሲጠበቅ የቆየ ብስራት እንደመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከስፍራው “እንኳን ደስ አለን” እንዳሉ ነበር ኤሊያስ መስረት የሚመራው መንጋ እሱ የፈበረከውን ዜና በ ” ሻሞ” የበተነው።

“ኢትዮጵያ ተጋበዘች እንጂ አባል አልሆነችም” ሲሉ ዜናውን በግልጽ ከማይታወቅ ፍላጎት መነሻ አራክሷል። ዓለም ሁሉ በይፋ ያወጀን፣ የብሪክስ ሰብሳቢ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት በየፋ በስብሰባው ላይ የተናገሩት መረጃ እያለ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋሽተዋል” ለማለት የሄደበት ርቀት በርካቶችን አነጋገሯል።

የዓለም ዓቀፍ ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው ኤሊያስ መሰረት በህልውና ዘመቻው ወቅትም ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መረጃዎችን ሲያሰራጭ እንደነበር በመግለጽ በርካቶች “ካሁን በሁዋላ እንዴት እንመንህ፣ መንግስትን መጥላትና ሃቅ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው። ዜናው ከኢትዮጵያ አንጻር እንጂ ከግል ስሜት የሚታይ አይደለምና” ወዘተ የሚሉ ትምህርታዊ አስተያየቶች ሙያውን ከማያውቁ ከማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቹ ተሰንዝሮበታል።

በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ኢትዮጵያን ብቻ ሳትሆን አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን በአዲስ አባልነት እንደተቀበሉ ታውቋል። በዚህም የአባል አገራቱ ቁጥር አስራ አንድ ደርሷል። BRICS በብራዚል፣ ሩስያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተቋቋመ ጥምረት እንደሆነ ነው።

አሁን ላይ ይኸው ቡድን ወደ ጂዖ-ፖለቲካ ኃይልነት በመቀየር ‘ የምዕራባውያኑን ተፅዕኖ ለመገዳደር ያስችለናል ’ የሚለውን መፍትሄ ለማበጀት እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ይህንን ቡድን ለመቀላቀል በርካታ ሀገራት ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበረ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም አንዷ ጠያቂ ነበረች። BRICSም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎችን ሀገራት በይፋ ተቀብሏል።

See also  አማራ ረሳ?

አዳዲሶቹ አባል አገራት ከጥር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ ጥምረቱን እንደሚቀላቀሉ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ አስታውቀዋል።

የሀገራችን ኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የBRICS ጉባኤ ኢትዮጵያን በአባልነት ተቀብሎ ማፅደቁን ተከትሎ “ይህ ለሀገራችን ታሪካዊ ሁነት ነው ” ሲሉ ተነግረዋል። ” ኢትዮጵያ ሁሉን አካታች ለሚሆን የበለፀገ የዓለም ስርዓት መስፈን ከሁሉም ጋር ለመስራት ሁሌም ዝግጁ ናት ” በማለት ለፍትሃዊ የዓለም መስተጋብር ኢትዮጵያ ያላትን እምነት አመላክተዋል።

BRICS አዳዲስ አባል ሀገራትን መቀበሉን ተከትሎ አጠቃላይ አባላቱ አስራ አንድ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል። እነሱም ፦

ብራዚል ፣ሩስያ ፣ህንድ ፣ ቻይና ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ አርጀንቲና ፣ ግብፅ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ኢራ ፣ ሳዑዲ አረቢያ ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ እንደሆኑ ዝርዝሩ ያስረዳል።

“ኢትዮጵያ አባል አልሆነችም፣ ገና ተጋባዥ ናት” በሚል ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጥላቻ ያላቸው ክፍሎች ዜናውን ለማጣጣል ጊዜ አልወሰዱም። ኢትዮጵያ ይርዚህ ታላቅ ጥምረት አባል መሆኗ ያበሳጫቸው እስኪመስል ዜናውን ከማራከስም አልፈው ሃሰት እንደሆነ ለማስመሰል የሞከሩም አሉ። ዜናው ዓለምን የዞረና ታዋቂ ሚዲያዎች ሳይቀሩ የተቀባበሉት እውነት መሆኑንን ከተረዱም በሁዋላ እነዚህ ክፍሎች ይቅርታ አልተየቁም፣ ማስተካከያም አላደረጉም። ይህንኑ የብስጭት የሃሰት ዜና ሳይመረመሩ የተቀባበሉና በላይክና ሼር የተባበሩ ለወድፊቱ ትምህርት የሚወስዱበት ዜና እንደሆነ በርካቶች ገልጸዋል። ዜናውንም “እንኳን ደስ አለን” ሲሉ አወድሰውታል።

ጥቂት ስለ ብሪክስ

  • የብሪክስ የመጀመርያው ስብሰባ እኤአ በ2009 በሩሲያ ነበር የተካሄደው
  • “ ብሪክስ” የሚለው መጠሪያ የብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን የመጀመሪያ ፊደል በመጠቀም የተፈጠረ ነው።
  • የብሪክስ አባል አገራት 40 በመቶውን የዓለም ሕዝብ ይይዛሉ።
  • አምስቱ አገራት በጋራ ያላቸው ምጣኔ ሃብታዊ አቅም ደግሞ የዓለምን 26 በመቶ ይሸፍናል።
  • የብሪክስ አባል ሀገራት የጂ 20 አባላት ሲሆኑ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ቻይና ደግሞ በህዝብ ብዛት፣ በቦታ እና በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከአለም አስር ግዙፍ ሀገራት መካከል የሚያሰልፋቸው ነው
  • አባል አገራቱ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ውስጥ ለመሠረተ ልማት እና ለዘላቂ ልማት ፕሮጀክቶች ሃብት የማሰባሰብ ዓላማ ያለውን ‘ኒው ዲቨሎፕመንት ባንክ’ (ኤንዲፒ) በ2014 አቋቁመዋል
  • መቀመጫውን ሻንግሃይ ቻይና ያደረገው ይህ ባንክ ትኩረቱን በንጹህ ኃይል፣ በትራንስፖርት መሠረተ ልማት፣ በውሃ እና ንጽህና፣ ዲጂታል መሠረተ ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ማኅበራዊ መሠረተ ልማት ላይ ያደረገ ነው።
  • ባንኩ በአባል አገራቱ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የመሠረተ ልማት የገንዘብ አቅርቦት ክፍተት ለመፍታት ያለመ ነው።
  • ኢትዮጵያ፣ አረብ ኢምሬትስ፣ ግብጽ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራን እና አርጀንቲና የብሪክስ አባል ሀገር ሆነዋል።
See also  ሽመልስ አብዲሳ“ዳግም ቃሌን አድሳለሁ”

ከብሪክስ ዋና ዋና ግቦች መካከል ጥቂቶቹ

  • ንግድን ማበረታታት፣ በአባላት መካከል እድገትና ትብብርንና የ BRICSን የገበያ ተደራሽነት ማሻሻል።
  • ለአባል ሀገራት መሰረተ ልማቶች እና የልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማትን መፍጠር።
  • በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ንግግሮችን እና ቅንጅቶችን ማጠናከር፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ልውውጦችን፡ የእርስ በርስ ግንኙነቶችን ማሳደግ እና አንዱ ለሌላው ባህል መከባበር እና በአባል ሀገራት መካከል ማህበራዊ እና ባህላዊ ልውውጦችን ማሳደግ።
  • በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ዘርፎች አለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር፣ በአባል ሀገራት መካከል የእውቀት ልውውጥን፣ የአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ እድገቶችን ማጠናከር።
  • ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት በጋራ በመስራት ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ እና ዘላቂ የልማት ዘዴዎችን ማስተዋወቅ።
  • እንደ ሽብርተኝነት ያሉ የጋራ የደህንነት ጉዳዮችን እና ስጋቶችን በመፍታት ሰላም፣ መረጋጋት እና ደህንነትን በአባል ሀገራትና በአለም አቀፍ ደረጃ ማረጋገጥ።
  • በታዳጊ አገሮች መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማካፈል እና ለሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋፅዖ የሚያደርጉ የSouth-South Cooperation ውጥኖችን መደገፍ ናቸው።

ምንጭ: ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረምና ዊኪፔዲያ


Leave a Reply