ያ – ሰፈር በሽሮ የሚፈተጉ በከሎች ? ዘይት ብርቅ ነው?

ያ- ሰፈር ትዝ አለኝ። ያ ሰፈር ድህነት ነው። ራሱ ድህነት ትርጉሙ ያ ሰፈርን ነው። ተሰብስበው ነዋሪዎቹ በህግ ደረጃ አልረቀቁትም እንጂ ድንች ከተገዛ አይላጥም። ድንገት ልጣጩ ከተገኘ የቀደም ይበልዋል። ስጋ ሲያምር ቢላ ማፏጨት እርካታ ነው። አብትና እናት ያላቸውን መብት ልጆች አይገኙም። ከአናት እስከ እግር ድረስ በአንሶላ ተጠቅልሎ እግር ሳይታጠፍ እንደ አስከሬን የሚተኙ ልጥጥ ይባላሉ። ያ ሰፈር ቁንጅና የፈሰበት ነው። ሃብታሞች ዘራቸውን ረጭተውበታል።

ዘይት አልጋ ስር መደበቁን ሰሰማ የእማማ ሰፈር ታወሰኝ። ዘይት አያውቁም። ፓንትና እሳቸው አልተገናኝቶም። ማቁላላት ተርስቷል። የመመገቢያ ማብሰያዎች በተሰቀሉበት ጥቀርሻ ለብሰዋል። በቴሌ የቀድሞ ቋንቋ “አገልግሎት ምስጫ ክልል ውጭ ሆነዋል” ማለት ይቀላል። እንደምን ከረማችሁ። እናንተ የድሃ ቀመኞች ልብ ይስታችሁ!! ወሬ ቸርቻሪ፣ አቃጣሪ የአገር መሪዎች መጥኔ ለናንተ። ከአህያ ቆለጥ ጠባሾች ጋር መስጥራችሁ ለምትዝርከረኩ ተጎራጆች ጥናቱን ይስጣችሁ!! ያበደው አንድ ቀነ እማማ ምድጃ ስር …

ጥያቄ – ምግብ ይሸምታሉ?

መስልስ- ቆየሁ። እዚችው (ቤታቸው መካከል ያለውን ጉልቻና አመድ እያሳዩኝ) እርመጠመጣለሁ። አለወጣም ..

ጥያቄ – ታዲያ ምን ይበላሉ?

መልስ – አዲስ አበባ የደግ አገር ነው ይቀልበኛል…

ጥያቄ – ይህ ግቢ የማን ነው?

መስልስ – አበል ይሰጠኛል። ዘጠኝ ብር በወር። በጃቸው እየተቆሙ አሁን አራጊውም ፈታሪውም እነሱ ናቸው ( እማማ ትርፍ ተብሎ አንድ የሚያከራዩት ቤት ተወስዶባቸዋል። ቤቱን ከቀበሌ የተከራየው ሰው እንዴት እንደሆነ ባይታወቅም ግቢውን የግሉ አድርጎ ለጠቅላይ ውርስ የእማማን ሞት የሚጠብቅ ባለጊዜ አጥሮና ምርጥ ቤት ገንብቶበት ይታያል )

ጥያቄ – እማማ ልብስ አለዎት? የውስጥ ሱሪ ገዝተው ያውቃሉ? ስጋስ

መልስ – ሰላሳ አመት አለፈኝ። የውስጥ ሱሪ የለኝም። ልብስ ከገዛሁ ቆይቷል። ስጋ አልክ?

ይህ ያበደው በአንድ ወቅት ከአንድ ሞት እንኳን ጨክኖ አልወስድ ካላቸው እናት ጋር ያወጋው ነው። እማማ የተናገሩት ሁሉ ህሊናን ያደቃል። እንዲህ ያሉ እናቶች፣ ልጆቻቸውን በቀይ ወይም በሌላ ሽብር ያጡና “እህህ” እንዳሉ የሞቱ ስት ይሆኑ? በእንደዚህ ያሉ ላይ ቆምረው፣ ክህደት ፈጽመውና ክፉ አድርገው በቁም ሞተው የተወገዱ፣ በግፍ በሰበሰቡት ላይ ሆነው የእርም ኑሮ የሚገፉ … ያበደው ያ ሰፈር ታወሰው።

See also  በተዓምር ካልሆነ እንዴት? የነቀዘ...

እዛ ሰፈር በፈረቃ ይተኛል። አባትና እናት ብቻ ናቸው ( ሁለቱም ካሉ) ፈረቃው የማይመለከታቸው። እህት ስትሸቅል ወንድም ይተኛል። እህት ከሽቀላ ቀንቷት ወይም ጡሃራ ማቷት ስትመለስ ወንድም ማረፊያ አስረክቦ ይወጣል። እንዲህ የሚኖሩ አዲስ አበባ አሉ። ያበደው የሰማውን ሁሉ አሰላ። አብላላ። ወዲያው ሌላ ሰፈር ታወሰው።

ይኽኛው ሰፈር እርም ቀለቡ ነው። ሞራል የሚባል የለም። ህሊና የሚባለው የሚዛን በትራቸው ተሰብሯል። ቆመው ሲሄዱና ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ሲስቁ የተመቻቸው ከመምሰላቸው ውጪ በቁም የሞቱ ተንቀሳቃሽ አስከሬኖች ናቸው። በተለይ አሁን ላይ ያበደው እነዚህ ሲያስባቸው … ሰው ይነግዳሉ። ከዛኛው ሰፈር በፈረቃ የሚተኙትን በቁንጅና እየመረጡ እንደ ዶሮ በሽሮ ያሳጥቧቸዋል። እንደ ዶሮ ገላባቸው በፈላ ውያ ተነጭቶ፣ በቀሰም ተነፍተው በጭድ አየለበለቡም እንጂ ድህነቱና የሰፈራቸው ሽታ እንዲራገፍ፣ በሽሮና በሎሚ ይፈተጋሉ።

ተፈትገው ሲያበቁ መሞላቀቅን ጨምሮ መስተንግዶ ይማራሉ። ገና ቦግ ማለት የጀመሩ ህጻናትን ” ላላቸው” በማቅረብ ብር የሚያፍሱ የዚያን ሰፈር ልጆች እንዴት እንደሚቸበችቡ ሲናገሩ አያፍሩም። አንድ ቀን እንዲህ ሆነ።

ታዋቂው መላጣ ሃብታም ቦሌ አካባቢ ካለው መልከስከሻ ቤት ብቅ አለ። አንዱ ወሲብ አቅራቢ ” በከል ሊበላ ነው” አለ። በከል ህጻን በግ ወይም ፍየል ማለት ነው። ስጋቸውም፣ አጥንታቸውም የሚበላ። ሰውየው ወደ ዱባይ ሊሄድ ነው። ዱባይ የሚሄደው ለንግድ አይደለም። በከል ከአዲስ አበባ ጭኖ ሄዶ ዱባይ በልቶ ቆዳ መስል ይዞ ሊመጣ … በሽሮ የተፍትገው የጸዱ በከሎች!!

ቪዛውም ትኬቱም በከሏም ቀረቡላት፣ በኩራት ፈገግ ብሎ ወደ መኪናው ሄደ። የልጅ ልጁን የምትሆን ህጻን ጭኖ በረረ። ይህ መጋኛ በቲቪ ቀርቦ ስለወጣቱ የወደፊት ተሳፋ አስተያየት ሲሰጥ ያበደው አይቶታል። ቦሰናም ታሪኩን ታውቅ ነበርና ” እመብረሃን …” በምርቃት ዋጋውን ሰጥታዋለች። በቅርቡ እንደተሰማው ከሆነ በልጆቹ አልተባረከም።

አብይ አህመድ ይን ታሪክ ይወቁት አይወቁት ግልጽ አይደለም። ሌቦች በበኤተስባችሁም በረከት የለም ብለዋል። አሜሪካ ብዙ ያሳያል። ውድ ቤቶች ውስጥ ዶላር ከፈረንጅ በላይ እየበተኑ የሚተፉ ውሪዎች ይታያሉ። በቲፕ አሰጣጥ አንደኛ ናቸው። የሚሸከሙት ዶላርና እነሱ የሰማይና የምድር ናቸው። ያ የዲሲ ቀበሮ ልጆች ሳይሆን አባቶቻቸውም አብርው ሲነከሩ አይቷል። ሆቴል ደጅ መሄድ አቅቷቸው እንደ እባብ ሲጎተቱ ያያቸው መኮንኖችም አሉ። ኢትዮጵያ ከምትለምነው በላይ የምትዘረፍ፣ ከምታግተው በላይ የምትታለብ ….

See also  ሱዳን - በጫጉላ ሰረገላ - "ሳምሪዬ ሳምሩ" አዲሱ ዘፈን ለትህነግ

ዛሬ ኑሮ ጨሷል። ዘይት አበይት ጉዳይ ሆኗል። ድሮ እናቶቻቸው መደብ ስር ወርቅ ሲቀብሩ የነበሩ መዥገሮች ዛሬ ዘይት አልጋ ስር መቅበር ጀምረዋል። ዘይትን በማናር ደሃውን ህዝብ ለብሶት እየነዱት ነው። ደሃው ዘይት ተወደደ ብሎ እንዲነሳ እየገፉ ነው። በዛ በኩል ነጫጭቦቹ መከላከያ ወረዳ ይሰሩላቸዋል። በዚህ በኩል እነሱ ዘይት ስር ይንደባለላሉ።

ተሳካ ቢባል፣ ብልጽግና በነውጥ ቢወድቅ ከመቃብር የሚወጡት እነማን ናቸው? ወልቃይት ይሰማል? ደሴና ኮምቦልቻ ጆሮህ ክፍት ነው? ኦሮሚያ ተኝተሃል? ሶማሌ አብዲ ኢሌ ናፈቀህ? … ቦሰና ” ሙሴ” ትላለች። ሙሴ በፈርዖን ቤት አድጎ እስራኤላዊያንን እየመራቸው ነጻ ሲያወጣ ” አንሄድም” አሉት። ቆሙ። ከሰማይ ከሚወርደው መና ይልቅ የግብጽ ሽንኩርት ናፈቃቸው።

እማማ ሞተዋል። እማማ ሳይሞቱ የቀማቸው ስለመኖሩ ያበደው መረጃ የለውም። የሰው ነጋዴዎቹ ዛሬ ባለሃብት ሆነዋል። እንደሚሰማው ግን ዋና ታንኳቸው ተሰብሯል። ሁሉም ቢኖሩም ውስጣቸው እንኳን በሽሮ በበረኪና የሚጸዳ አይደለም። …

ከዛም ከዚህም ይተኮሳል። ማንን ከማን ለማዳንና ማንን ምን ላይ ለመተካት እንደታለመ ግልጽ ባይሆንም በየድስፋራው ማረፊያው የማይታወቅ ጩኸት አለ። ጩኸቱን የሚያሟሙቁ አቅጣሪ የአገር መሪዎችም አሉ። ሾካካ፣ አቃጣሪ ሹመኞች በመድረክ ሲረቱ በዩቲዩብ ጉሊት ወሬ ይነግዳሉ? ፊትለፊት ወጥተው አይታኮሱም። “አንቱ ፣ የተከበሩ” የሚባሉትም አጀንዳ ሰፋሪ ሆነው ሲባትቱ …

ታዲያ እንዲህ ያሉ ወንፊቶችን ” አላምናችሁም። እናንተን እንደሰው ቆጥሬ አላወራም” የሚል መሪ በምን ሂሳብ ይወቀሳል? በምን ሂሳብ ይሰደባል? ያበደው ቦሰና ያለችው ትዝ አለው። የብልጽግና ፓርቲ መቀመጫ አዲስ አበባና ፊንፌኔ መሆኑ በድብቅ ተውስኗል። ሲሉ የትህነግ የአሜሪካ ተውካቶች መምሬ ሃብታሙ ተናገሩ። መምሬ ከአቃጣሪው ከሰሙት ሚስጤር መካከል አንዱ መሆኑንን ገልጸዋል።

ቦሰና “ጥርሴስ ልማዱ ነው” አለችና አይኗን እንዳይስቅ ሰግታ ” ብልጽግና ጽህፈት ቤቱን ኪንያ ቢያደርግ ምን አገባቸው?” ስትል ጠየቀች። በዚህ አላበቃችም። በህገ መንግስቱ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት። ብልጽግና ኦሮሚያ ቢሮ አለው። ባህር ዳርም አለው። ትግራይም አለው። ስለዚህ አዲስ አበባና ፊንፌኔ ቢባል ነውሩ ምንድን ነው? የቦሰና ጥያቄ ነው!!

See also  [የሽግግር መንግስት] ሊቋቋም ነው !!

ጉዳይ የፓርቲው፣ ከዛም በላይ የአባቱ እንጂ የሊሎች ሊሆን እንዴት ቻለ? ይህ ምኑ ሚስጢር ነው? ያበደው እየሳቀ ወጣ። የቦሰና ቡና ጅንጅብል ስላለበት ምላስ ይማታል። ሲነሳባት አሽሙሯ ሃይለኛ ነው። “ዝም ስንል” ካለች ታወደዋለች። ከጀመረች የሚያስቆማት የለም። ግን ምሉስ ናት። ስታንባርቅ ደጎል ተፈናጥሮ ከቤት ይወጣል። የዛኔ ” በሞትኩት” ትልና ይቅርታ ጠይቃው ዝም ትላለች።

ደጎል መፈክር ጠሩ ነው። ከኢቲቪ ጋር ተላምዷል። 360 ዞሮ የሚስቅባቸው አሉ። መረጃ አይናቅምና የብልጥጥ ያያቸዋል። የተኮለኮሉትን ስለመታዘቡ የሚያውቀው እሱ ብቻ ነው። የእማማን ነብስ ይማር። የዘይት ቀባሪዎችንም ነብስ ይማር። ያልሞቱ ሙታኖችንም ነብስ ይማር። መርዝ የሚያመርቱ በቀቀኖችም… “እናሸንፋለን” የሚሉትንም ነብሳቸውን በአጸደ እንደስራቸው ያኑርልን።

ግን ዘይት ብርቅ ነው? ዘይት!! ያለ ዘይት የሚበሉ ሁሉ በዘይት መብላት ጀመሩ? መለሰ ዜናዊ ስኳር አጠረ ሲባል ” ድሮ ስኳር የማይጠቀም አርሶ አደር ስኳር መጠቀም በመጀመሩ ነው” ብለው ነበር። ፈጣሪ በሚገባቸው መጠን ይማራቸው። እሳቸው አርፈዋል። መጽሃፋቸውን የዋጡ አላረፉም። “በጨውና በውሃ የሚመገበው ህዝባችን ዘይት እያንጨፈጨፈ መብላት በመጀመሩ ዘይት አጠረን” የሚል ዛሬ ድረስ የመልስን መንፈስ የሚገባር ብልጽግና ብቅ እንዳይል ቦሰና ሰግታለች። አሁን መሸ። ነገ ብርድ ይሁን ሙቀት አይታወቅም። ቀኑ ሲፈልገው ፋኖ፣ ሲፈልገው ፋናኝ ይሆናል። ግን … ግን ይልና ያበደው ይሸበለላል።

Leave a Reply