ኢዜማ እስር ላይ ያሉት የድርጅቱ መሪ ዶክተር ጫኔ ከበደ የድርጅቱን መርህ መጣሳቸውን በይፋ አስታወቀ። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ከድርጅቱ መርህ ውጭ ባፈነገጠ መልኩ መንቀሳቀስ ኢዜማን እንደማፍረስ እንደሚቆጠር አስታውቋል። የድርጅቱን መርህና አሰራር የዘርዘረው መግለጫ ” የፓርቲያችን ሊቀመንበር ጉዳይም ከዚህ ከላይ ከተገለፀው መርኅ አንጻር የሚታይ ይሆናል ሲል ፓርቲያችን ይገልፃል” ሲል አቋሙን ይፋ አድርጓል። <<…ከሰላማዊ ትግል እና ከዜግነት ፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውጭ ያለን የፖለቲካ እንቅስቃሴ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ መደገፍ፣ የሀሳብም ሆነ የተግባር ተሳትፎም ሆነ ትብብር ማድረግ ከኢዜማዊነት መርኅ ማፈንገጥ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን::>> ብሏል
ኢዜማ ከሰላማዊ የትግል ስልት ውጪ በዘውጌ ብሔርተኝነትም ሆነ አፈሙዝ በታከለበት የትግል መንገድ መንቀሳቀስን ድርጅቱ የቆመበትን መርኅ መቃረን አድርጎ ያየዋል። ማንኛውም የኢዜማ አባል ብሎም ከወረዳ እስከ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ድረስ የሚሳተፍ አመራር ከዚህ የድርጅቱ ፅኑ ዕምነት ውጭ የተንቀሳቀሰ እንደሆነ ድርጅቱን ለማፍረስ እንደሚሰራ ተደርጎ እንደሚቆጠር መታወቅ አለበት። ኢዜማ ውስጥ የማይነካም ሆነ የማይተካ አባልም ሆነ አመራር የለም! ስለሆነም ከድርጅቱ ዓላማ እና የትግል መስመር ባፈነገጠ መንገድ በሚንቀሳቀሱ አባላቱ ላይ የፀና አቋም ይይዛል።
ኢዜማ የሊቀመንበሩን መታሰር በተመለከተ የሰጠው መግለጫ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም የፓርቲያችን ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደ በጸጥታ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋልን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ጉዳዩን በጥንቃቄና በትኩረት እንደሚከታተለው፣ መረጃዎችንም በተከታታይ እንደሚያሳውቅ መግለፁ የሚታወስ ነው፡፡
በዚሁ መሠረት የፓርቲያችን ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይህንኑ ጉዳይ እንዲከታተል የሰየመው ኮሚቴ ባደረገው ማጣራት ዶ/ር ጫኔ ከበደ በቁጥጥር ስር የዋሉት በፓርቲያችን ባላቸው ኃላፊነት ሳይሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በኮማንድ ፖስቱ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ መሆኑን መረጃዎች አግኝተናል፡፡
ይህ መረጃ ከተገኘ በኋላ የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚው ኮሚቴ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ተወያይቷል።
በአሁኑ ወቅት ሃገራችንን ሰቅዞ የያዘው የፖለቲካ ውጥረት መነሻ በሁለት እሳቤዎች መካከል በሚደረግ ፅንፍ የረገጠ መካረር መሆኑ እሙን ነው ፡፡ በአንድ በኩል በእውቀት፣ እውነት፣ መርኅ እና ምክንያታዊነት ምሶሶዎች ላይ የተመሠረተው የዜግነት ፓለቲካ፤ ከዚህ በተለየ ደግሞ ተበደልኩ፣ ተገለልኩ፣ የሚገባኝን ያህል የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና የፖለቲካ ውክልና ተነፍጎኛል . . . ባህሌን፣ ቋንቋዬን እና ወግ ሥርዓቴን ማሳደግ አልቻልኩም በሚሉ በዘውግ ላይ በተንጠለጠለ ልዩነትን መሰረት ባደረገ የማንነት ፖለቲካ መካከል ሲደረግ የቆየው ግብግብ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ነው ብለን እናምናለን።
በሁለቱ የፖለቲካ መስመሮች መካከል የሚደረገው ትንቅንቅ የሚያስከትለውን የሕይወት እና የንብረት ውድመት፣ በአጠቃላይ ህዝባችንን ከችጋር እና ጉስቁልና በሚያላቅቅ የልማት ሥራ ላይ መዋል ያለበት ውስን የሀገር ኃብት ብክነትን በማስቀረት ከትጥቅ ትግል ይልቅ በመተማመን ላይ የተመሠረተ የሃሳብ ትግል (በሰላማዊ ንግግር ችግሮችን መፍታትን ልንከተለው የሚገባ ብቸኛ የትግል ስልት) እንደሆነ የሚያሳይ አቋማችንን ደግመን ደጋግመን የገለፅነው የአደባባይ ሃቅ ነው።
ኢዜማ በመርኅም ሆነ በተግባር በዜግነት የፖለቲካ አስተሳሰብ እና በፀና የሰላማዊ ትግል መስመር የሚያምን፣ ይህንኑ መርኅ ብቻ ተከትሎ የሚሠራ፣ በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ በዘውግ ተኮር የፖለቲካ እንቅስቃሴም ሆነ በኃይል መንግሥታዊ ሥልጣን ለመያዝ በሚደረግ ትግል ውስጥ ፈጽሞ የማይሳተፍ ብቻ ሳይሆን በዚህ መንገድ ተጉዘን ዕረፍት ለናፈቀው ህዝባችን የሰላም አየር ልናመጣለትም ሆነ በዘላቂነት ወደተረጋጋ የፓለቲካ ሥርዓት ልንደርስ እንደማንችል ያለጥርጥር የሚያምን ድርጅት ነው፡፡
ኢዜማ ከሰላማዊ የትግል ስልት ውጪ በዘውጌ ብሔርተኝነትም ሆነ አፈሙዝ በታከለበት የትግል መንገድ መንቀሳቀስን ድርጅቱ የቆመበትን መርኅ መቃረን አድርጎ ያየዋል። ማንኛውም የኢዜማ አባል ብሎም ከወረዳ እስከ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ድረስ የሚሳተፍ አመራር ከዚህ የድርጅቱ ፅኑ ዕምነት ውጭ የተንቀሳቀሰ እንደሆነ ድርጅቱን ለማፍረስ እንደሚሰራ ተደርጎ እንደሚቆጠር መታወቅ አለበት። ኢዜማ ውስጥ የማይነካም ሆነ የማይተካ አባልም ሆነ አመራር የለም! ስለሆነም ከድርጅቱ ዓላማ እና የትግል መስመር ባፈነገጠ መንገድ በሚንቀሳቀሱ አባላቱ ላይ የፀና አቋም ይይዛል።
ኢዜማዊነት በምንም መንገድ ሁለት የማይታረቁ ሃሳቦችን እያጣቀሱ መሄድን የማይፈቀድ እንደሆነ መላው የድርጅታችን አባላት፤ እንደዚሁም በክብር፣ በነፃነት እና በእኩልነት የመኖር ዋስትና እንዲረጋገጥለት ዘወትር የምንታገልለት መላው የኢትዮጰያ ህዝብ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን።
ሀገራችን ከገባችበት የፖለቲካ ምስቅልቅል ደረጃ በደረጃ ልትላቀቅ የምትችለው በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የምንሳተፍ ኃይሎች (መንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪል ማኅበራት፣ የመገናኛ ብዙኋን፣ . . . እና መላው የሃገራችን ዜጎች) ሕጋዊ እና ሰላማዊ የሆነ ትግልን በመከተል እና ከዛ ውጪ ያለ አማራጭ የትግል መስመር ውስጥ ባለመሳተፍ እና ባለመደገፍ እንደሆነ እናምናለን። በተለይ በአሁኑ ሰዓት የሃገራችንን መሠረታዊ ችግሮችን ሥርዓት ለማስያዝ እንደሃገር ብዙ ተስፋ የሰነቅንበት ሃገራዊ ምክክር ሊጀምር በመሆኑ ትኩረታችን እሱ ላይ መሆን አለበት ብለን በጽኑ እናምናለን።
የሃገራዊ ምክክሩን ውጥኖች ተግባራዊነት በማረጋገጥ ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥታዊ ሥልጣን የሚያዝበት ብቸኛው መንገድ እንዲሆን፣ እና ከዛ ውጪ ያሉት አማራጮች በኢትዮጵያ ምድር የማይሞከሩ ብቻ ሳይሆኑ የማይታሰቡም ጭምር እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል ብለን እናምናለን።
በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ የሚገኙ አባላት እና ደጋፊዎች ከመርኀችን እና በግልጽ ካስቀመጥነው የሰላማዊ ትግል አቅጣጫችን በተለየ መንገድ መጓዝ የፓርቲውን ሕገ ደንብ በግልፅ መጣስ ከመሆኑም በላይ ከዘመን ዘመን ሲንከባለሉ የመጡ የሃገራችንን የፖለቲካ ችግሮቻችንም ሆነ ህዝባችንን አንገት ያስደፉ እና ለከፋ ድህነት እና ጉስቁልና የዳረጉ ስብራቶቻችንን በማባባስ ሂደት ላይ ከመሳተፍ ተለይቶ አይታይም።
ኢዜማውያን ይህን በውል በመገንዘብ ከሰላማዊ ትግል እና ከዜግነት ፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውጭ ያለን የፖለቲካ እንቅስቃሴ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ መደገፍ፣ የሀሳብም ሆነ የተግባር ተሳትፎም ሆነ ትብብር ማድረግ ከኢዜማዊነት መርኅ ማፈንገጥ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
የፓርቲያችን ሊቀመንበር ጉዳይም ከዚህ ከላይ ከተገለፀው መርኅ አንጻር የሚታይ ይሆናል ሲል ፓርቲያችን ይገልፃል።
መስከረም 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ
- ሰው ሰራሽ ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን መቀላቀል የኢትዮጵያ ሌላ አማራጭ?አርተፊሻል ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት ይችላል፤ ይህ በአለም ላይ በኢትዮጵያ የአፋር ምድር ረባዳነት የተነሳ ተፈጥሮ የሰጠው እድል ነው! በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል አርተፊሻል ቦይ በመስራት ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት መሆን ትችላለች፡፡ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሊፈጠር የቻለው፤ የኢትዮጵያ የአፋር ቦታ ከባህር ወለል በታች እስከ 110 … Read moreContinue Reading
- ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ቁጥጥሩን አጠንክሮ እንደሚገፋበት አስታወቀ፤ ህገወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ አለመረጋጋት ለመግራት የግንዘብ ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የተጀመረው ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑ ተመለከተ፤ ተጠናክሮ ክምሩ እንደሚሰራበትና ግሽበትን በዓመቱ መጨረሻ 20 ከመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተሰማ። ህገወጥ የወርቅ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና የማበረታቻ መደረጉ ለውጥ ቢያሳይም በቂ እንዳልሆነ ተመለከተ። … Read moreContinue Reading
- የኮሚሽኑ የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሙስና ክስ ጋር ተያይዞ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሆነየአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የአልባሳት ግዢ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ። ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ … Read moreContinue Reading
- መንግስት የነዳጅ ድጎማን በህገወጥ መንገድ ሲጠቀሙ ነበሩ ያላቸውን 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከስርአቱ አስወጣ፣ የሰርቁትን ይከፍላሉየታለመለት የነዳጅ ድጎማን ላልተገባ ዓላማ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርዓቱ እንዲወጡና ዕዳ እንዲከፍሉ መደረጉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህን ያሉት የመንግሥት የ2016 የመጀመሪያ የሩብ ዓመት አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት ነው። የግምገማው ተሳታፊዎች መንግሥት የነዳጅ ድጎማን ጨምሮ በርካታ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋገጡ ተግባራትን ማከናወኑን አድንቀው፤ ሆኖም” ድጎማው … Read moreContinue Reading
- በዓመት አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ የሚያመርተው ፋብሪካ ከመጋቢት በሁዋላ የሲሚንቶ ዋጋ ወደ ነበረበት የሚመልሰ ነውበቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ ያለውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ በመጋቢት ወር ይጠናቀቃል። ምርቱ በተባለው ወር ሲጀምር የሲሚንቶ ዋጋ አሁን ካለበት በግማሽ እንደሚወርድ ይጠበቃል። ከመጋቢት በሁዋላ ፋብሪካው በ50 በመቶ የሲሚንቶ እጥረቱን ያስወግዳል። ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ኩባንያ … Read moreContinue Reading