የአጥንት መሳሳት ምንድነው?

ምንም አይነት የህመም ስሜት ሳይኖረው ወይንም ምልክቶችን ሳያሳይ ለከፍተኛ የጤና ችግር ብሎም ለሞት ሊዳርገን የሚችለውን የአጥንት መሳሳት ችግር ምንድን ነው? 

ከሰውነት ክፍሎቻችን አጥንት ጠንካራው እና በቀላሉ የማይጎዳ ነው፤  ነገር ግን  አጥንት በመሳሳት ምክንያት ጉዳት ሊደርስበት ይችላል። አጥንትን ደካማ እና በቀላሉ ተሰባሪ የሚያደርገው የአጥንት መሳሳት ሕመም ነው።

 ለመሆኑ  የአጥንት መሳሳት ምንድነው?

 አጥንት ሁልጊዜ በለውጥ ላይ ነው፣ በቋሚነት ሴሎቹ ይሞታሉ ቀጥሎም ይተካሉ። የአጥንት መሳሳት የሚከሰተው አጥንት የመተካት አቅሙ ሲቀንስ ነው፤ ነገር ግን በብዛት የሚበልጠው መገንባቱ ነው።

የአጥንት መሳሳት ወንድ ሴት ሳይል ሁሉንም የሚያጠቃ ሕመም ቢሆንም ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። ሕመሙ ነጮች እና የሩቅ ምሥራቅ ሰዎች ላይ ይበረታል፤ በተለይ ደግሞ በዕድሜ የገፉ ሴቶች ላይ ይበረታል። ከአጥንት መሳሳት ጋር የተያያዙ ስብራቶች በአብዛኛው ወገብ፣ መዳፍ ወይም አከርካሪ ላይ ይስተዋላሉ።

 የአጥንቱ አሠራር በአንድ በኩል እየተገነባ በአንድ በኩል ሲፈርስ፤  የአጥንታችን ጥንካሬው ጤናማ ይሆናል። የማፍረሱ ሂደት ሲያይል ነው የአጥንት መለስለስ የሚመጣው።

 የአጥንት መሳሳት  ምልክቶች ምንድን ናቸው? 

 – በሽታው ገና ሲጀማምር ብዙ ምልክት አያሳይም፤ ነገር ግን አንዴ አጥንት ከሳሳ ወዲህ የሚከተሉት ምልክቶች ይታያሉ፡-

– የጀርባ ሕመም

– ከጊዜ በኋላ ቁመት መቀነስ

– መጉበጥ

– በቀላሉ የሚሰበር አጥንት

 አጥንት መሳሳት በምን  ምክንያት ይመጣል?

 የአጥንት መሳሳትን ሊያስከትሉ ከሚችሉ ምክንያቶች አንዱ ዕድሜ ነው፤ ነገር ግን አሁን አሁን  በወጣቶችም  ላይ  ይህ ችግር እያጋጠመ ይገኛል።

የቫይታሚን ዲ እና የካልሺየም እጥረት፤ እንዲሁም የእንቅርት በሽታ ለዚህ አይነተኛ መንስኤዎች ሊሆኑ  ይችላሉ።

የአጥንት መተካካት ሂደት ከ20 ዓመት በኋላ እየቀነሰ ይመጣል፤ እድሜ በጨመረ ቁጥር የአጥንት ክብደት እጅጉን ይቀንሳል በመሆኑም ተጋላጭነቱም ከፍ ያለ ይሆናል።

ሌላው በዘር፣ በአኗኗር ዘይቤ፣ አልኮል አዘውትሮ መጠታት እና ሲጋራ ማጨስም መንስኤዎቹ ናቸው።

የጤና ሁኔታ እንደ ካንሰር፣ የኩላሊት ወይም የጉበት በሽታ እና የተለያዩ መድሃኒቶችን መጠቀም  እንደመንስዔነት ይጠቀሳሉ። 

ውፍረት፣የመገጣጠሚያ ሕመም እና ለስላሳ መጠቶችን ማዘውተርም ሌሎች ምክንያቶች ሆነው ይነሳሉ።

See also  ወራሪው ትህነግ በአፋር ክልል ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ተቋማትና ንብረት አውድሟል

 የአጥንት መሳሳትን መከላከያ መንገዶች

የአጥንት መሳሳት ችግርን ለመፍታት በካልሺየም የበለጸጉ ምግቦችን  መመገብ፣  ጤናማ አመጋገብ እና አካዊ እንቅስቃሴዎች የአጥንት መሳሳትን ከመከላከሉም በላይ የሳሱ አጥንቶችን ያጠነክራሉ።

ወተት እና አሳ የመሳሰሉ ምግቦችን ማዘውተር እንዲሁም ጨው እና ቡና በልኩ መጠቀም ይመከራሉ፡፡ ክብደት መቀነስ፣ በቂ የጸሀይ ብርሃን ማግኘት እና የለስላሳ መጠጦችን መቀነስም እንደመፍትሄ ተቀምጧል፡፡ ከአልኮልና ከሲጋራ ሱስ ነፃ መሆን እንደሚገባም ባለሙያዎች ይመክራሉ።

የአጥንት መሳሳትና ህመም ህክምና

_ የአጥንት ማደርጃ መድሃኒት

_የስብራት ተጋላጭነት መቀነሻ መድሃኒት

_ስብራት የመጠገን ህክምና እንደሆኑ የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

መረጃዎቹን ከተለያዩ ምንጮች አግኝተናቸዋል

 በሜሮን ንብረት – ኢፕድ


 • በሶማሌ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ 28 ሰዎች ሲሞቱ ከ300,000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል
  በሶማሌ ክልል ከ33 ወረዳዎች በላይ ተከሰተ የተባለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው እርዳታ እያደረገ የሚገኘውን Save the Childrenን ጠይቋል። የድርጅቱ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አሕመድ በጎርፉ የተጎዱት ከ600,000 በላይ ሰዎች እንደሚሆኑና ከ300 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንና የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸዋል። ” ምግብም፣ … Read moreContinue Reading
 • የፕሮስቴት እጢ ምልክቶችና ህክምናው
  ፕሮስቴት እጢ በወንዶች ፊኛ በታች የሚገኝ ተፈጥሯዊ የሰውነት አካል ነው ፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ዩሮሎጂ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር መሀመድ አብዱልሀዚዝ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷የፕሮስቴት እጢ ዋነኛ ተግባር የዘር ፈሳሽ በማመንጨት ወደ ፊት ለፊት እንዲወጣ በማገዝ ለመራቢያነት ማገልገል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የበሽታው መንስኤ ብለን የምንጠራቸው ምክንያቶች … Read moreContinue Reading
 • ለተማሪዎች መውደቅ ማነው ተጠያቂው ?
  በህ/ተ/ም/ ቤት የሰዉ ኃብት ልማት ፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ፦ ” … ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊነቱን ወደራሱ መውሰድ አለበት በምንልበት ጊዜ ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የክልል ትምህርት ቢሮዎችን የሚመሩና እስከ ወረዳ እስከታች ድረስ እንዲሁም የትምህርት አመራሩ በትምህርት ቤት ደረጃ ምን ያህል Shock … Read moreContinue Reading
 • የአጥንት መሳሳት ምንድነው?
  ምንም አይነት የህመም ስሜት ሳይኖረው ወይንም ምልክቶችን ሳያሳይ ለከፍተኛ የጤና ችግር ብሎም ለሞት ሊዳርገን የሚችለውን የአጥንት መሳሳት ችግር ምንድን ነው?  ከሰውነት ክፍሎቻችን አጥንት ጠንካራው እና በቀላሉ የማይጎዳ ነው፤  ነገር ግን  አጥንት በመሳሳት ምክንያት ጉዳት ሊደርስበት ይችላል። አጥንትን ደካማ እና በቀላሉ ተሰባሪ የሚያደርገው የአጥንት መሳሳት ሕመም ነው።  ለመሆኑ  የአጥንት መሳሳት ምንድነው?  አጥንት ሁልጊዜ በለውጥ … Read moreContinue Reading
 • የደም ግፊት – ድምጽ አልባው ነብሰ ገዳይ
  ስለ ደም ግፊት የሚወጡ መረጃዎች አስደንጋጭ እየሆኑ ነው። ደም ግፊት እጅግ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች እየጨረሰ ነው። ደም ግፊት “ድምጽ አልባው ገዳይ” የተባለውም ለዚህ ነው። አሁን አለሁ ሲሉ ድንገት ጭጭ የሚያደርግ የዘመናችን መርዝ ነው። በመላው ዓለም 1,28 ቢሊየን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 79 ዓመት የሆነ ሰዎች ለከፍተኛ የደም ግፊት የጤና ችግር … Read moreContinue Reading

Leave a Reply