ትህነግ “ለደሴ ሕዝብ ፍቅር ስል ዘምቻውን ተውኩት”፤ የጄነራል ጻድቃን ጦር መከበቡ ተሰማ

የስነ ልቦና ጦርነቱ አይንን ሽቅብ በጦር ደንቁሎ “ትንኝ ጫረችው” አይነት ሆኗል። ከግንባር ከሚነገሩት የ”ድል” ዜናዎች ይልቅ ካድሬነት ዝር ያላለባቸው ምስኪን አርሶ አደሮች የሚሰጡትን ምስክርነት የመታመን አቅም አለው። ብዚሁ መመዘኛ ሲታይ ትህነግ በስፋት ይዟቸው ከነበረባቸው አካባቢዎች እንዲለቅ መደረጉ ሃሰት አይደልም። አሁን የተያዘው የማህበራዊ ሚዲያዎች ቅስቀሳ ግን ” የዋሁንና ንጹህ የሆነውን አርሶ አደር ወደ ጎን ጥላችሁ እኔን እመኑኝ” የሚል የካድሬ ድርቅና ነው።

አማራ ክልል እየተግለበለበ በሰው ልጆች ማዕበል በጥድፊያ ሲወረር ቅድሚያ ለማስተባበል ሞክሮ ነበር። ወዲያው ማመኑና መወረሩን በግልጽ መናገሩ ዛሬ ደቡብ ጎንደርን ሙሉ በሙሉ ነጻ፣ ሰሜን ጎንደርን ከማይጸብሪ የኮሪዶር ክፍት አትክፈት ፍትጊያ በቀር ነጻ አውጥቶ የቀረውን ወራሪውን ሃይል የወሎ ግንባር ለማስወገድ ጫፍ እንደደረሰ እየተነገረ ነው። መከላከያ ባለ ትልቁ ድርሻ መሆኑ ሳይዘነጋ!! መከላከያም በሙሉ ሃይል ማጥቃት መጀመሩን ይፋ አድርጓል።

በአፋር ክልልም ቢሆን ትህነግ የጅቡቲን መስመር ቆርጦ አዲስ አበባን እንደሚያንቅ ይፋ ቢያደርግም እስካሁን በተግባር የታየ ነገር የለም። ቦታ እየጠቀሱ ዝርዝር ሪፖርት ማቅረብ ቢያስቸግርም፣ በአፋርም በኩል ትህነግ ከያዛቸው ቦታዎች እንዲለቅ ተደርጓል። ዛሬን ጨምሮ። በወሎ ግንባር ለሽማግሌዎችና ወጣቶች “አርፋችሁ ተቀመጡ” የሚል መልዕክት ተበትኖ ነበር። “ደሴ ናፈቀችኝ” ሲሉ አቶ ጌታቸው በቀደም ድንቅ ግጥም ተቀኝተው ነበር። ዛሬ እንደሚሰማውና ከቦታው በምስል እንደታየው በወሎ ግንባር ደሴን የሚያሰጋ ነገር እንደሌለና ሙሉ ዋግ ነሳ ሆኖ ጦሩ ወደፊት እያቀና መሆኑንን ነው።


አቶ ጌታቸው “ደሴ ናፈቀችኝ” ካሉ በሁዋላ ረቡዕ ነሐሴ 26 አንድ የታገል ሰይፉ ግጥም ትዝ እንዳላቸው ጠሰው ይህን ከተቡ፤

“ጠላቴን ስመርቅ”

ከፍ ያርግህ ወደ ላይ ከስልጣኑ ስማይ

ያድርግህ ከፍ ከፍከዚያ የወደቅክ’ለት

ኣጥንትህ እንዳይተርፍ


ከመንግስት መገናኛዎች ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የወሎ ግንባር የጦር መሪ፣ ” በሁለኡም ግባር ተመሳሳይ ድል እየተመዘገበ ነው። በቅርቡ ወደ ጉድጓዳቸው የሚገቡ ይመስለኛል” ሲሉ ተደምጠዋል። ይህን ያሉት ” ለደሴ ሕዝብ ካለን ክብር በመነሳት የደሴውን እቅዳችንን ሰርዘናል” በሚል አቶ ጌታቸው ማስታወቃቸው ተገልጾ ኢሳት ግንባር ተገኝቶ ሲጠይቃቸው ነው። በአፋር በኩል በተመሳሳይ ትህነግ መመታቱ ሲገለጽና በርካታ ምርኮኞች ሲያዙ ” ለአፋር ወንድም ሕዝብ ስንል ዘመቻውን ትተነዋል” በሚል መገሃድ መገለጹ ይታወሳል።

See also  ቱርክ - 296 ሰዓታት በፍርስራሽ ውስጥ
ዝርዝሩን እዚህ ላይ ይመልከቱ

ያለ የለለ ሀይሉን በወሎ ግንባር ያሰለፈው አሸባሪው ህወሓት በወገን ጦር በተወሰደበት እርምጃ መዳከሙን የወሎ ግንባር የኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌ/ጀኔራል ሀሰን ኢብራሂም አስረድተዋል። “በጋይንት እና በጭፍራ አካባቢዎች የደረሰበትን ሽንፈት በወሎ ግንባር አካክሳለሁ ብሎ አሸባሪው ሃይል በርካታ ሀይል አሰልፎ የነበረ ቢሆንም ሙት እና ቁስለኛውን እንኳን ሳያነሳ ወደኋላ እየሸሸ ነው” ብለዋል።

በተለይም የውጫሌ ግንባርን ለመስበር ተደጋጋሚ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም በመከላከያ ሰራዊት ተመቶ ወደኋላ በመሸሽ ሌላ ሀይሉን ደግሞ በተሁለደሪ፣ ሰግለንና ወረባቦ አካባቢዎች የውጊያ ግንባርን ፈጥሮ ነበር ብለዋል ጀነራሉ።

ይህም እቅዱ የወገን ጦርን አቅጣጫ ለማስቀየር በመሆኑ የተወሰነው ሰራዊት እና ልዩ ሀይሉ እንዲሁም ሚሊሻውና የአካባቢው ፖሊስ ተቀናጅተው በመመከት ከፍተኛ ኪሳራ እንዳደረሱበት ሌ/ጀኔራል ሀሰን ኢብራሂም አስታውቀዋል። ጠላት ከፍተኛ የሰው ቁጥር በማሰለፍ የወሎ ግንባርን ለመስበር ተደጋጋሚ ማጥቃት ቢያደርግም በመከላከያ፣ በልዩ ሀይልና በሚሊሻው በሚወሰድበት እርምጃ ወደኋላ መሸሽን ብቸኛ አማርጭ እንዳደረገ አመልክተዋል።

ይህ ትህነግ ይዤዋለሁ ያለውና ኤርሚያስ ተኩማ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደላኩለት ጠሶ ትናንት በቴሌግራም ገጹ የለጥፈው የሃይቅ ከተማ ፎቶ ነው። ” ወያኔ ትላንትናና ዛሬ ወሎ ላይ የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ የሐይቅ ከተማ ህዝብ ደስታውን ሲገልፅ አምሽቷል” ሲል ነው እፎቶው ግርጌ የጻፈው።

የአሸባሪው ሀይል በወገን ጦር በከፍተኛ ሁኔታ ተመቶ በጊራና አካባቢ ወደኋላ ሲሸሽም ትዋጋለህ አልዋጋም በሚል በከባድ መሳሪያ የታገዘ የርስ በርስ ውጊያ ውስጥ ገብቶ እንደነበርም ጀነራሉ ተናግረዋል።የሽብር ቡድኑ በሸሸበት ሁሉ በመከታተል እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑንም አስታውቀዋል። በመከላከያ በኩል በዝርዝር መረጃ ቢሰጥም በትህነግ በኩል ዝርዝር መረጃ ይህ እስከታተመ ድረስ አልወጣም። ይሁን እንጂ ደሴን ለመያዝ የነበረው እቅድ ” ለወንድም የደሴ ህዝብ ሲባል ተሰርዟል” የሚል ሃሳብ ተሰንዝሯል።

“የተረጋገጠ የድል ብስራት መረጃ ” ወረባቡ የገባው ጁንታ በተባበረ ክንድ FDRE Defense Force – የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፤ በፌደራል ፖሊስ ፣ በአማራ ልዩ ሃይል እና በአካባቢው ሚሊሻና ህዝብ ተጠራርጎ እንደ ቅጠል እረግፎ የተረፈውም እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል። እኛ ምኞታችንም ፍላጎታችንም ይህ ወራሪ ቡድን የውሎ…. በሚል ከስፍራው ለኤርሚያስ ቶኩማ የተላከ ፎቶ ነው

በሰሜን ጎንደር ያለውን የጦርነት ግለት አስመልክቶ ስታሊን “በሰሜን ጎንደር እና በአፋር ጭፍራ በኩል የሰማነው ይኸው ነው። አሳዛኝ ቢሆንም መነገር አለበት” ሲል ሌተናል ጀነራል ባጫ ” ይቀፋል። ነገር ግን መነገር ስላለበት እንናገራለን” እንዳሉት አድርጓል። በሰሜን ጎንደር በአንድ ቀን 18 የማጥቃት ሙከራ የተደርገበትን የኮሪዶር ማስከፈት ውጊያ ሙሉ በሙሉ በኪሳራ እንደዘጋው የክልሉ አስተዳደሮች፣ ሚሊሻዎችና የመከላከያ የቅርብ አዋጊዎች አስታውቀዋል።

የትህነግ ደጋፊዎች በዚሁ መስመር ድል እንደቀናቸው ቢናገሩም የተዘጋውን የሲዳን መውጪያ ኮሪዶር እንዲከፈት ከመወትወት አልታቀቡም። በማይጸብሪ ሁመራ ግንባር እንደሚሉት ድል የተመዘገበ ቢሆን ኖሮ ኮሪዶር የማስከፈት ጫናው እጅግ ተጠናክሮ ባለቀጥለ ነበር ሲሉ የሚከራከሩ አሉ። በግንባሩ ተደጋጋሚ ጥቃት በመሰንዘር ኮሪዶሩን ለማስከፈት ሙከራ እንደሚደረግ የመከላከያ መኮንኖች አይክዱም። ነገር ግን ሊሳካ አለመቻሉን ነው ያስታወቁት። አሁንም ተደጋጋሚ ሙከራ የማድረግ ሙከራ ከሱዳን በሚነሳ ሃይልና በትህነግ ሃይል እንደሚከናወን ይጠቅሳሉ።

See also  በአማራ ክልል የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ችግርአለ፤ የጥቁር ገቢያ ሽያጭ አንዱ ፈተና ነው

የአገር መከላከያ በትናትናው ዕለት በይፋ መልሶ ማጥቃቱ ተጠናክሮ እንደሚከናወን ካስታወቀ በሁዋላ ትህነግ ወደ ማይጨው መስመር የመገስገስ ሃስብ እንዳለ ማወቁንና መንግስት ለዳግም ወረራ መዘጋጀቱን አስታውቆ ሕዝቡ እንዲጠነቀቅ አሳስቧል። ቀደም ባሉት ሳምንታት አሶሲየትድ ፕረስ አላማጣና ኮረም ከትሀንግ እጅ መውጣታቸውን ታማኞች እንደነገሩት ገልጾ መዘገቡ ይታወሳል።

ትህነግ አለበት የሚባልበት ቦታና የአገር መከላከያ ሰራዊት አልፎ ግብቶባቸዋል የሚባሉት ስፍራዎች፣ የአማራ ሃይልና በአፋር ግንባር ከበባውን እያጠበበ የመጣው ሃይል አሰላለፍ በርካቶች የጦር ሜዳው ዜና ሙሉ በሙሉ እንደሚቀየር ግምት እንዲያሳድሩ አድርጓቸዋል።

በሰሜን የማይጸብሪ ግንባር ለማጥቃት የሚመጣውን ሃይል እየጠበቁ መምታት እንዳለ ሆኖ ከጀርባ የጀነራል ጻድቃን ሃይል መከበቡ ተሰምቷል። ይህ ሃይል ከተበተነ በዛ መስመር ያለው ሃይል የሱዳን ድነበርን ከሚተብቀው በስተቀር ወደ ሙሉ ማጥቃት ስለሚሸጋገር ከበባውን ለማስለቀቅ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነ ታውቋል። ከአፋርና ከወሎ ግንባር ወደ ትግራይ የሚያቀናው ሃይል የዚህን ውጊያ ውጤት እየተተባበቀ ስለመሆኑም ተሰምቷል። ይሁን እንጂ ነጻ ወገን አልረጋገጠውም።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በዚሁ ስሙ በረሃ ኖሮ፣ መንግስት ሆኖ፣ ተመልሶ በረሃ ገብቶ አሁን ትግራይን እየመራ ነው። ትህነግ ሰሞኑንን ቅድመ ሁኔታ አንስቶ መደራደር እንደሚፈልግ ለበርካታ አገራትና ለተባበሩት መንግስታት ደብዳቤ ደጋግሞ ልኳል። ጉዳዩ በሰላም እንዲያልቅ የሚመኙ ውሳኔውን በበጎ ቢያዩትም ህግ የሚፈልጋቸው የትህነግ አባላትን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆነና መከላከያን ካረደ ሃይል ጋር ተቀምጦ መደራደር እንደሚከብድ እያመለከቱ ነው። ምንም ይሁን ምን ተጨማሪ ውድመትና ኪሳራ ሳይከተል፣ ኢኮኖሚውም ከዚህ በላይ ሳይሽመድመድ በስምምነት ሰላም ማውረድና ለአወዛጋቢ የድንበርና የክልል ጉዳዮች ፖለቲካዊ የአስተዳደር ቅርጽ የመከለስ መፍትሄ እንዲበጅ የሚያሳስቡም ጥቂት አይደሉም።

የተፈናቀሉ፣ በተያዘው የምርት ዓመት ያላረሱና ለችግር የተጋለጡ ቁጥራቸው ከፍተኛ በመሆኑ መጪው ዓመት ይበልጥ ችግሩ ሊሰፋ እንደሚችል ካሁኑ እየተገለጸ ነው።

Leave a Reply