አሸባሪው ህወሃት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎና በጎንደር የህዝቡን የኢኮኖሚ መሰረቶች ማውደሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ህዝቡን ለመከራና ስቃይ በመዳረግ ዳግም ወደ ፖለቲካ ስልጣን ለመምጣት አደገኛ ሙከራ ውስጥ የተዘፈቀው ላለፉት 27 አመታት ስልጣን ላይ የነበረው አሸባሪው ቡድን፤ አብዛኛው የትግራይ ክልል ህዝብን ከሴፍቲኔት ተረጅነት እንኳን ሊያላቅቅ አልቻለም፣ ቡድኑ ለክልሉ ህዝብም ደህንነት ያለውን ግዴለሽነት በተደጋጋሚ አሳይቷል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሸባሪ ቡድኑ በወረራቸው የሰሜን ወሎና ጎንደር አካባቢዎች ያደረሰው መጠነ ሰፊ ውድመት የአማራ ህዝብ ጠላትነቱን ዳግም ያስመሰከረበት መሆኑን ገልጿል።
በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች የሚወጡ ሪፖርቶች እንዳመለከቱት የብዙ ቤተሰቦች የኢኮኖሚ አቅሞችን አውድሟል፤ በወረራቸው አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች የአሸባሪው ታጣቂዎች የደረሱ ሰብሎችን እየዘረፉ ማመልከታቸውን ጠቅሷል።
“አርሶአደሩ ያከማቸው እህል ተዘርፏል የቀረውም እንዲወድም ሆኗል፤ የእርዳታ እህል ማከማቻ መጋዘኖች የአሸባሪው ቡድን የዘርፋ ሰለባ ከመሆናቸው ባሻገር ከተረጂዎችም ይቀማል” ብሏል መግለጫው፡፡
ቡድኑ ያስከተለው መጠነ ሰፊ ውድመት በግለሰብ ላይ ብቻ ሳይሆን እንደማህበረሰብ የህዝብ መገልገያዎችን የህፃናት መዋያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች፣ ባንኮች፣ የጤና ማዕከላት፣ ሆቴሎችና ሎሎችም ተቋማት ወድመዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን ስጋት ላይ ጥሎት አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንዲወስድ ያስገደደው? ከሆነም ህብረቱ ይህን አቋሙን ለምን በይፋ ከማስታወቅ ይታቀባል? ነገሩ በዚህ ደረጃ አሳሳቢ ከሆነ ቢያንስ ሁለት መስመር መግለጫ እንዴት ማውጣት ተሳነው …. ብዙ መወያያ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል የዕዳ ጫናን ለማቃለል ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት ሪፖርቱ የቀረበለት ፓርላማ አሳስቧል። ዜና ፓርላማ እንዳለው የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል ያለበትን የዕዳ ጫናን ለማቃለል ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ በሀገራችንም የሽግግር ፍትህ አስፈላጊነት ታምኖበት ፖሊሲ ሲዘጋጅ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ ፖሊሲ ተጠናቆ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀ ሲሆን ይህ አጭር ፅሁፍ ፖሊሲው በያዛቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ይሆናል፡፡ የፖሲው ይዘት አወቃቀር የፖሊሲው በመግቢያ በሀገራችን በተለያዩ ዘመናት… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ደብዳቤ የሚሊሻ ሃይሉ ጸጥታ በማስከበሩ ስራ መውጪያ መግቢያ እየለየ ውጋት ስለሆነባቸው ተላቶች ሆን ብለው ከቅዠት የተነሳ ያሰራጩት እንደሆነም አመልክተዋል። ከሰሞኑ በአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አማካኝነት እንደተጻፈ እና ለሁሉም ዞኖች እና ከተማ አሥተዳደሮች… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
በግንባታ ሂደት ላይ ያለው የአዋሽ ወልዲያ ሃራ ገበያ የባቡር መንገድ ፕሮጀክት ሃላፊነት በማይሰማው አሸባሪ ቡድን የጥቃት ሰለባ ሆኗል ፡፡
“ሽብር ቡድኑ የሚያስከትላቸው መጠነ ሰፊ ውድመቶች ለትግራይ ህዝብ የሚፈይድለት ነገር እንደሌለ ይታወቃል፤ ይልቁንም የትግራይና የአማራን ህዝብ ወደ ባሰ ስቃይና እንግልት ያስገባል” ሲል ሚኒስቴሩ አመልክቷል፡፡
የሽብር ቡድኑ በሰሜን ወሎ እንዲሁም በጎንደር የፈፀመውና እየፈፀመ ያለው ውድመት በፖለቲካው አለሁ ለማለት የሚደረግ የመጨረሻው መፍጨርጨር እንደሆነም ነው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በችግር ውስጥያሉና እገዛ የሚሹ በሰሜን ወሎና ጎንደር ያሉ ህዝቦችን ትኩረት እንዲሰጣቸው የጠየቀው መግለጫው፤ ወራሪው በያዛቸው አካባቢዎች ያሉ ዜጎች የተፋጠነ የሰብአዊ እርዳታ እንዲደርሳቸው ጥሪ አቅርቧል።
Ena