በአማራ ሕዝብ ዝክረ ታሪክ ማዕከል ውስጥ ቅሬታ ይነሳበት የነበረው ኃውልት በአዲስ ተሰርቶ ተመረቀ

ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ የሰማዕታት መታሰቢያ በሚል ሐሳብ በተቋቋመው የ”አማራ ሕዝብ ዝክረ ታሪክ ማዕከል” ውስጥ ቅሬታ ይነሳበት የነበረው ኪነ ኃውልት በአዲስ ተሰርቶ ተመረቀ፡፡ የማዕከሉ ስያሜም ከሰማዕታት ኃውልት ወደ የ”አማራ ሕዝብ ዝክረ ታሪክ” በሚል ተተክቷል።

ማዕከሉ የአማራ ሕዝብን ሥነ ልቦና፣ ታሪክ እና ማንነት የማይወክሉ የኪነ ኃውልት ክፍሎችና የታሪክ መገለጫዎች ያሉበት ነው በሚል ነበር በክልሉ ምክር ቤት የታኅሣሥ 2013 ውሳኔ ኃውልቱ ፈርሶ ሕዝቡን በወጉ በሚወክል ትዕምርት እንዲተካ የተወሰነው።

በዚህም ለዓመታት በማዕከሉ ውስጥ መሳሪያና አንገት ደፍቶ መቆሙን የሚያሳያው ኃውልት እንዲፈርስ ሆኖ በአዲስ ተተክቷል።

አዲሱ ኃውልትም የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ ቁመና በሚመጥን መልኩ ተሰርቶና ወካይ መገለጫ ሆኖ መመረቁ የተገለፀው።

You may also like...

Leave a Reply