ፍትሕ ሚኒስቴር ከ32.9 ሚሊዮን ብር በላይ አስመለሰ፣ ከ2ሺህ ካሬ በላይ ህገወጥ ቦታ አሳገደ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ግማሽ አመት ዕቅድ አፈጻጸም በወንጀል የተገኘ ሃብትን ከማስመለስ ጋር በተገናኘ በተለያዩ ወንጀሎች የተሳተፉ ግለሰቦችን ንብረት ለይቶ እንዲታገዱ በማድረግ በሕጋዊ መንገድ ለመንግስት እንዲመለሱ ማድረግ ችሏል፡፡

ለአብነት በተለያዩ 13 ጉዳዮች ሀያ ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ሰባት መቶ ስድሳ አራት ብር ከሃምሳ ስምንት ለመንግሰት ገቢ እንዲደረግ ለማስወሰን የተቻለ ሲሆን በሶማሌ ክልል በተፈጸመ ወንጀል በፍርድ ቤት በተሰጠ የውርስ ትዕዛዝ በፍርደኛ ስም የሚገኝ 3,375,000 እና በድርጅቱ ስም የሚገኝ 6,240,828.61 በድምሩ 9,615,828.61/ዘጠኝ ሚሊዮን ስድስት መቶ አስራ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከስድሳ አንድ ሳንቲም ለሶማሌ ክልል ገንዘብ ቢሮ ገቢ እንዲደረግ ተደርጓል፡፡ በአጠቃላይ ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ስድስት ብር ከአስራ ዘጠኝ ሳንቲም ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡

እንዲሁም 2,209 ካሬ የታገደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1,999 ካሬው እንዲወረስ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲጥበት በማድረግ በመሬት አስተዳደር አማካኝት ወደ መሬት ባንክ በመግባት ሂደት ላይ ይገኛል።

ከታገዱ ንብረቶች ጋር ተያይዞም 8 ድርጅቶች፣ ገንዘብ 1,406,592,626.43 ብር፣ 32,516,111.42 ሼር፣ 233 ተሸከርካሪዎች፣ 80 ቤቶች እና 114 ማሽነሪዎች ናቸው፡፡

ተቋሙ በቀጣይም በታገዱት ላይ ተገቢውን ክርክር በማድረግ በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ንረቶቹ እንዲወረሱ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዲደረጉ የሚያደርግ ሲሆን በህዝብ ጥቆማ እና በራስ ተነሳሽነት የተመዘበሩ ሀብቶችን በህግ አግባብ እየመረመሩ ለመንግስት እንዲመለሱ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ይህንኑ ተግባር በውጤታማነት ለማዝለቅም ተቋሙ በወንጀል የተገኙ ሀብቶችን በማስመለስ ላይ የሚሰራ እራሱን የቻለ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል መመስረቱም ይታወቃል፡፡

Federal general attorney

You may also like...

Leave a Reply