የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በአሸባሪው 11 የአልሸባብ የሽብር ቡዱኑ ከፍተኛ አመራሮችና 70 ታጣቂዎችን ደመሰሰ!

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በአሸባሪው የአልሸባብ ቡድን ላይ በወሰደው እርምዳ 11 የሽብር ቡዱኑ ከፍተኛ አመራሮችና 70 ታጣቂዎችን ደመሰሰ!
ጀግናው የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ሰራዊት በኢትዮጵያና ሶማሊያ ድንበር በተለይም በሶማሊያ በኮል ዞን ዬድ ወረዳ በሚገኘውና ልዩ ስሙ “ቁዳሌ”በተባለው አካባቢ በነበረውን የአሸባሪው አልሸባብ የሽብር ቡድን ታጣቂዎች መቀመጫ ላይ በወሰዱት የታቀደና የተቀናጀ ጥቃትና ኦፕሬሽን በሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ የሽብር ቡዱኑን ካምፕና መሳሪያዎችን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠረ።

ጀግናው የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል በአሸባሪው ቡዱን ላይ በወሰደው ጥቃትና እርምጃ የሽብር ቡድኑ 11 ከፍተኛ አመራሮችና 70 ታጣቂዎችን በመደምሰስ በድጋሚ ታሪክ ሰርቷል።

የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በሶማሊያ ቦኮል ዞን “ቁዳዓሌ” በተባለ መንደር ውስጥ ተሰባስበው ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ዝግጅት በሚያደርጉትበት ወቅት የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ሰራዊት በወሰደው  የተቀናጀና የተደራጀ እርምጃ ነው የተደመሠሡት።

በጀግናው የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል በትናንትናው አለት የተገደሉ የአሸባሪው የአልሸባብ ታጣቂዎች ከፍተኛ አመራሮች
****

1. አደን መዶቤ- በሽቡር ቡዱኑ አጠራር (አሚር ሳሪዮ ከፍተኛ አመራር)

2. ሰላሁዲን ከፍተኛ መኮንንና የሽብር ቡድኑ የፈጥኖ ደራሽ ታጣቂዎች መሪ (በሽቡር ቡዱኑ አጠራር አሚር ሳሪዮ(ከፍተኛ አመራር)

3. አህመድ ዴሬ  (የሽብር ቡዱኑ የኢትዮጵያ ክንፍ ብለው የሚጠሩት አቡ ዙቤር ምክትል ኃላፊ)

4. ሼክ መሀመድ ኸይር ሰላድ (በሶማሊያ ቦኮል ዞን የሽብር ቡድኑ የፈጥኖ ደራሽ ታጣቂዎች አዛዥ)

5.መሀመድ ሁሴን ጉሞው (በቅፅል ስሙ ሁሴን ኢትዮጵያ) ከፍተኛ አመራር በሽብር ቡድኑ አጠራር አሚር ሳሪዮ።

6. መሀመድ ድሪዬ  (ከፍተኛ አመራርና በሽብር ቡድኑ አጠራር ምክትል አሚር ሳሪዮ)

7. አብዱረህማን ሃጂ – (የሽብር ቡድኑ የህግ፣ የምልመላና የግንዛቤ ሀላፊ)

8. ሀሰን ሙክታር (ከፍተኛ አመራርና በቅርቡ በኤልበርዴ በተደረገ ውጊያ የቆሰለ

9. አሊ መሲራ -ከፍተኛ አመራር

10. አብድረዛቅ መሀመድ አብድረህማን በቅፅል ስሙ አካ ሰንዴሬ የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ መኮንን

11. መሀመድ ኢልባድ- ከፍተኛ አመራር

See also  የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የመኪና መገጣጠሚያ ማዕከል ሊገነቡ ነው

ልዩ ሀይሉ ለ10 አመታት በአሸባሪው የአልሸባብ ቡድን ስር የነበረችው የሶማሊያ ቦኮል ዞን ስር የሚትገኝ “ረብ ዱሬ ከተማን ነፃ በማውጣት የሀገርን ዳር ድንበር አስከብሯል።

በመጨረሻም የሶማሌ ክልል ልዩ ዋና አዛዥ ጀነራል አብዲ አሊ ሰይድና ሌሎች መኮንኖች ህዝቡን በሰላም ዙሪያ በማወያየት ላይ ናቸው።
ምንጭ፦ የሱማሌ ክልል ኮሚኒኬሽን

Leave a Reply