የትህነግ ወኪሎች ከመንግስት ጋር ዳግም በናይሮቢ ውይይት ጀምረዋል

የኢትዮጵያ መንግስት እና የትህነግ ከፍተኛ ተደራዳሪዎች በኬንያ ሶስተኛውን የሰላም አማራጭ ውይይት መጀመራቸው ተሰምቷል። በመጅመሪያው የፕሪቶሪያ ስምምነት ትጥቅ እንደሚፈታና መንግስቱን እንደሚያፈርስ ያመነው ትህነግ ታጣቂዎቹን መቀለ አካባቢ ካሉ ከአራት ግንባሮች ማንሳቱን ከማስታወቁ በቀር ሌሎቹን ውሎች ተጋባራዊ ስለማድረጉ ያለው ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መንግስትና የትግራይ ኃይሎች ከፍተኛ ተደራዳሪዎች በናይሮቢ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ውይይት ለማድረግ ወደዛው ማቅናታቸውን የአፍሪካ ህብረት አስቀድሞ ማስታወኡ ያታወሳል።

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ትግበራ በተመለከተ የሚደረግ እንደሆነ የተነገረለት ውይይት ከዛሬ ረቡዕ እስከ ዓርብ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚቆይ ሲሆን መንግስት ውይይቱን በጥብቅ እንደሚፈልገው፣ በውሳኔው መሰረት ትህነግ ባስቸኳይ ወደ ተጋራዊ እንቅስቃሴ እንዲያመራ በአደራዳሪዎቹ ፊት መንግስት ጠንካራ አቋም እንደሚይዝ ኢትዮ12 ሰምታለች። መንግስት ለመቀለ ህዝብ ደህንነት ሲባል አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ባስጠነቀቀበት በቀናት ውስጥ ውይይቱ መጠራቱ የዚሁ ማረጋገጫ እንደሆነ ነው ዜናውን የነገሩን ያስረዱት።

በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት የኢትዮጵያ መንግስት እና የትህነ ተወካዮች በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን ይህንን ስምምነት ተከትሎ የሁለቱም ተዋጊ ኃይሎች ዋና አዛዦች በናይሮቢ ኬንያ ተገናኝተው በትጥቅ መፍታት እና የሰብአዊ እርዳታ ዙርያ ላይ ውይይት በማድረግ ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል።

በዚሁ ስምምነት መሰረት በሁሉም አቅጣጫ በአየር ጨምሮ ትግራይ ስንዴ፣ ዱቄት፣ዘይርት፣ ቁሳቁስ፣ መድሃኒትና ነዳጅ በብዛትና በስፋት መሰራጨቱን፣ እየተሰራጨ እንደሆነና ጀምሩ የሚወደስ እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት ሳይቀር በይፋ አስታውቋል። የትህነግ ሊቀመንበርም መሻሻል መታየቱን አምነዋል። ለዚህም ይመስላል መንግስት ከሁለት ቀን በፊት ” እንጥፍጣፊ ሳይቀር” ሲል ለሰላም ስምምነቱ የሚጠበቅበትን እየተወጣ እንደሆነ አመልክቷል።

ትህነግ “ወራሪ” ስለሚለው፣ ነገርግን በሃይሉ ነጻነቱን ያወጀውን የአማራና ሃይል፣ እንዲሁም የኤርትራ ጦር ከትግራይ ክልል መውጣት አስመልክቶ ሃላፊነቱ የመንግስት በመሆኑ ትህነግ ትጥቁን ፈቶ ለጎረቤት ክልሎችና ለኤርትራ ስጋት መሆን የማይችልበት ደረጃ እስካልደረሰና አቅሙ ልክ እንደሁሉም ክልል ካላደረገ ጥያቄው ተቀባይነት እንደማይኖረው የመንግስት ግልጽ አቋም እንደሆነ ይታወቃል። ትህነግ አማራ ወረር ያለውን አካባቢ በስም የማይጠቅስ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ራሱ ትህነግ በሃይል ወሮ ከፍተኛ ግፍና ጄኖሳይድ ፈጽሞባቸዋል የሚባሉትን አካባቢዎች የሚጠይቅ ከሆነ ግልጽ ሊያደርግ እንደሚገባ፣ ለዚያም ግልጽ ምላሽ እንደሚሰጥ በርካቶች እየጠየቁ ነው።

See also  ትህነግ ለድርድር ባቀረበው ቅድመ ሁኔታ ኦሮሞ ተባባሪዎቹን ከዳ "ደግ አደረጉ፤ ዋጋቸውንም ሰጣቸው"

ባድመና አካባቢውን በተመለከተ አቶ መለስ ዜናዊ ምክር ረግጠው ይግባኝ በሌለው ፊርማ በትህነግ ስም ሄደው ለኤርትራ ያስረከቡት፣ ከዛሬ አራት ዓመት በፊትም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ የአልጀርሱን ስምምነት በመተግበር ከኤርትራ ጋር ሰላም እንዲወርድ ውሳኔ የሰጠበት በምሆኑ ” አንድም የመከላከያ አባልም ሆነ የአገር ሃብት ባድመን አስመልክቶ ሊባክን አይገባም” የሚል አቋም በህዝብ ዘንድ የጸና አቋም እንደሆነ በተደጋጋሚ ተመክቷል። አቶ መለስ ዜናዊና ድርጅታቸው ትህነግ በባድመ ጦርነት ላስፈጃቸው ከሰባ ሺህ ለሚልቁ የኢትዮጵያ ልጆች ክብር ሳይኖራቸው ባደባባይ አገርን ላወረዱበት ጉዳይ ዛሬ መንግስት ከኤርትራ ጋር የሚጣላበት ምክንያት እንደማይኖር በርካቶች ያምናሉ። ይህ ጉዳይ ለውይይቱ የሚቀርብ እንደሆነ ተመልክቷል። ዓላማው ኢትዮጵያንና ኤርትራን ለማጣላት በመሆኑ መንግስት እጅግ በጥንቃቄ የሚፈጽመውና የሚያየው እንደሆነ፣ ይህ እንደ ማስያዣ ተውስዶ ትጥቅ አልፈታም የሚለው አካሄድ ተቀባይነት እንደማይኖረው ኢትዮ 12 ሰምታለች። መንግስት እጅግ የከረረና ቀነገደብ የተቀመጠለት ውሳኔ እንዲወሰን ቁርጥ አቋም መያዙን፣ መከላከያ በጥጥርሩ ስራ ያደረጋቸው አካባቢዎች ዳግም ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት አለመያዛቸውና ራሳቸውን በአዲስ አደረጃጀት ማደራጀታቸው ምን አልባትም ትህነግ እግደረደራለሁ ቢል መንግስት በጉልበት መቀለ ለመግባት ማስረጃና መረጃ የሚይዝበት ውይይት ከመሆን እንደማያልፍ ነው ዜናውን ያጋሩን ያመልከቱት።

ለሶስት ቀናት ይቆያል የተባለው ይህ ውይይት በዝግ እንደሚካሄድ እና በማጠቃለያው ላይ መግለጫ እንደሚሰጥ ቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።በውይይቱ ላይ የቀድመው የኬንያ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን የአሜሪካ መንግሥት፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) እና የአፍሪካ ህብረት ተወካዮችም እንደሚሳተፉ ተዘግቧል።

በትግራይ 80 በመቶ መብራት የጀመረ ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት የባንክ አገልግሎት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅቱ መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።

Leave a Reply