ከአማራ ክልል ብጥብጥ ጀርባ “የኦርቶዶክስ እምነት”ለምን? ደወል የሚስደውሉ አባቶችን ማን ነው የሚመራቸው፣ የሻዕቢያ ዝምታስ?

ይህ ጽሁፍ መልካም አባቶችን፣ ለፈጣሪያቸው ያደሩ ምዕመናኖችን ፈጽሞ አይመለከትም። ይህ ጽሁፍ ኢትዮጵያን በጸሎታቸው የተሸከሙ አባትና እናቶችን እንዲሆም ደጋግ የጸሎት ሰዎችን ያከብራል። ይህ ጽሁፍ መስክቀልን ለእይታ የተሸከሙትን ሳይሆን መስቀሉን ከልባቸው አኑረው ለሚኖሩበት ልዩ ክብር ይሰጣል። ጽሁፉ የሚጠይቀው በቀጥታ ዕምነቱ ከሚፈቅደው ውጪ በመገዳደል ትግል ውስጥ ተዘፍቀው ደውል የሚደውሉና ሰላማዊ ህዝብን የሚያስጨርሱ፣ ለዓመጽ የሚቀሰቅሱና ዓመጽ ጠማቂዎችን በሚሸሽጉና ቀለብ በሚያዘጋጁ መናጢዎች ላይ ነው።

ልብ እንበል። የትግራይ ኦሮቶዶክስ “በቃኝ” ሲል “ቀኖና ተጣሰ” ብሎ አደባባይ የወጣ፣ ጥቁር የለበሰ፣ መግለጫ ያንጋጋ አልተሰማም። እንደውም ” የራሳቸው ጉዳይ ጥንቅር ይበሉ” ነው የተባለው። ኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ” በቃኝ” ሲል “ቀኖና ተጣሰ፣ የጫካ ሲኖዶስ…” በሚል ሰማይ ምድሩ ተገለባበጠ። ሰልፍ፣ ማስጠንቀቂያ፣ ውግዘት … ጥቁር ልበሱ…” ተባለ። የቀኖና ጉዳይ ከሆነ ለኦርቶዶክስ በትግራይና ኦሮሚያ ሲኖዶስ መካከል እንዴት ልዩነት ታየ? እንደ ክርስቲያን ሲታይስ ይህ ልዩነት ቀድሞውኑ ሃይማኖታዊ ነበር? እንደው ንጽሁ ህሊና ላላቸው ይህ ጥያቄ ቢነሳ መስቀል የተሸከሙት “አባቶች” ምን ይመልሳሉ? ከሁሉም በላይ ” ለምን የኢየሱስን ስም ጠራችሁ” ብሎ እግር ተወርች ጨለማ ቤት ውስጥ አስሮ የሚያበሰብሰው የኢሳያስ አፉወርቂ መንግስት እንዴት ግብጽ ድረስ ሄዱ ለኦርቶዶክስ ንቅናቄ አጋርነቱን አሳየ?

አሁን እንደሚሰማው መከላከያ ሰላም ለማስከበር ሲንቀሳቀስ አንዳንድ ቤተ ክርስቲያናት ደወል እየደወሉ ሰላምዊ ህዝብ እንዲወጣ እያደረጉ ነው። ታጣቂዎችንም ሸሽገው እንደሚይዙ ምስክሮች እየተናገሩ ነው። ቤተክርስቲያን በዚህ ደረጃ ለምን ጣልቃ መግባት እንዳለባት ግልጽ ያልሆነላቸው መልካም አባቶች ይህን ድርጊት ወደ ምክርና ሰላም አባትነት ሊቀይሩት እንደሚገባ እየገለጹ ነው። ይህ ትግል በቤተክህነት ድጋፍ ማግነቱ ሌሎች የዕምነት ተከታዮችን ስጋት እየጭመረ ነው።

የአማራ ሕዝብ ተፈርጆ፣ ያለስሙ ስም ተበጅቶለት ላለፍት ሰላሳ አመታት በደል ደሶበታል። ይህ ታላቅ ሕዝብ ትህነግ የሚባል ድርጅት ገና ሲፈጠር ጀምሮ ከሻእቢያ ጋር ሆኖ ፈርጆ አስገድሎታል። አፈናቅሎታል። በየቀኑ ዘመቻውን እያተናከረና በሬ ወለድ ድርስት እያዘጋጅ የሚፈራ፣ ወራሪ፣ ግፈኛ አድርጎ ስሎታል። የዚህ ሁሉ ክምር ፕሮፓጋንዳ አሁን ደርስ ይህን ህዝብ ዋጋ እያስከፈለው ነው። ይህ አከራካሪ ጉዳይ አይደለም።

ከለውጡ በሁዋላ ወደ ትግራይ ያፈገፈገውና ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ላይ እሳት ሲያነድ የከረመው ትህነግ በቅጥረኞችና በመንጋ ተከታዮቹ ከፍተኛ ሃብት በማፍሰስ በጅምላ ቪዲዮ እየቀረጹ የሚገድሉ ነብሰበላዎችን ቀጥሮ በጅ አዙር ስልታን ላይ እያለ ከሚፈጽመው በላይ አማራን አሳርዷል። አፈናቅሏል። ይህ ሁሉ ሲሆን በማህበራዊ ገጾችና ከአገር ውስጥ እስከ ውጭ አገር በዘረጋው የሚዲያ ኔት ዎርክ ለቅስቀሳ ተጠቅሞበታል። በቀደምው መዋቅሩ ውስጥ በስብሰው ከሚዳፍቁት ውጭ የሆኑት መሪዎች ለማጠልሸት ተጠቅመውበታል። ተሳክቶላቸዋል። በቀድሞ የትህነግ ብስብሻ ላይ የቆሙ ዛሬ ድረስ ይህንኑ የቆየ የሙት አደራቸውን ለመወጣት መከረኛውን ህዝብ በክረምት እንዳያርስ፣ በረሃብ እንዲመታ፣ ነገ ለማኝ እንዲሆን ጦርነት ቀስቅሰውበታል።

አሁን የተከፈተው ድፍን ጦርነት እነማን እንደጎነጎኑት ያታወቃል። መከረናዋና አመድ አፋሽዋ ኢትዮጵያ መሃል እምብርቷ ላይ ሆነው ዶላር በሚያጥቡ፣ ኮንትሮባንድ በሚነግዱ ትታለባለች። የቅባት ዕህሉ፣ ነዳጁና ማዕድኑ በኮንትሮባንድ ማጋበሱ አልበቃ ብሎ ነገሮች መስመር እንዳይዙ ትርምስ ይጠነሰስላታል። የወቅቱ ተረኛ የሆነውን የአማራ ህዝብ ብሶት በማጎን ” አራት ኪሎ ግባ” በሚል መፈክር አደረጃጀቱ ቤተ ክህነት ላይ የተከለ፣ ወይም ምሽግ ያደረግ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ቆይቷል።

See also  እንዲህ ባለ ሁኔታ አጨብጭቤ ቀረሁ

የኦርቶዶክስ ዕምነትና የሻለቃ ዳዊት ህብረት

የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች ሆነው ጨዋ። ልባቸው ቅን። ደጎች። ለአገር የሚያነቡና ፈርሃ እምላክ ያላቸው እጅግ ብዙ ናቸው። መልካም አባቶችና መሪዎችም እንደዚህ ብዙ አሉ። የሚአነቡ የአገራቸው ብርሃን የሆኑ መነኩሴዎች አሉ። የዛን ያህል ደግሞ በክፋት መስመር ሆነው ቤተክርስቲያኗን የሚነዱ፣ ምዕመኑንን መስቀል እያሳለሙና እያሳዩ የሚያሳስቱ አሉ። ጽሁፍ እነዚህን ብቻ የሚመለከት ነው

” አሁን የወሬና የማንቃቱ ስራ አልቋል” ሲሉ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ውስጥ ቀኖ መታሱን በመቃወም ረብሻ ከመነሳቱ በፊት ሻለቃ ዳዊት አውስትራሊያ ተገኝተው ተናግረው ነበር። ሰፊ ሚስጢር ይፋ በሆነበት የአውስትራሊያ ንግግራቸውን ተከትሎ ” የኦሮሞ ቤተ ክህነት አፈነገጠ” በሚል ተቃውሞ ጎነ። ይህ ከመሆኑ ሳምንታት በፊት ጀርመን የሚኖረው ዘመድኩን አሜሪካ ተገኝቶ ከነ ሻለቃ ጋር መክሮ ነበር። ራሱ ፎቶ እየቀያየረ አሜሪካ በሸነና ማለቱን ሲያስታውቅ አምልጦት ይፋ ያደረገው አሳቡ ላይ ይህን ጉዳይ ገሃድ አመልክቷል።

የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ከዋናው ኦርቶዶክስ በኩርፊያም ይሁን በሴራ ማፈንገጡንና የራሱን አካሄድ እንደሚከተል ካስታወቀ በሁዋላ ” የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ተጣሰ” በሚል የተናበበ መግለጫ (ቤተ ክርስቲያን አዘጋጀችው ለማለት የሚያዳግት) ሲሰራጭ፣ ዛሬ ሻለቃ ዳዊት ለሚመሩት ንቅናቄ ድጋፍ የሚሰጡ ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች፣ የሚታወቁ ፖለቲከኞች፣ ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ የረንጓዴ ቢጫ ቀይ ካባ ለባሾች፣ አርቲስቶች፣ ታውቂ ሰዎች ነን የሚሉ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ቢሮ አስከላክዮች፣ የመንግስት ሚዲያዎች፣ የንግድ ተቋማትና የባንክ ሰራተኞች … ጥቁር ለብሰ ” ቤተመንግስት ግባ” ብለው ያሰሙት ድምጽ ” የትግራይ ኦርቶዶክስ ቀኖና ጥሶ ሲሿሿም ምነው ዝም አሉ?” የሚል ጥያቄ ሲነሳ መልሳቸው ምንድን ነው? ሊንኩን ተጭነው እባክዎን ያድምጡ

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=679117810243712&id=100004114531430&sfnsn=mo

“እንግዲህ ጉዳዩ የዕምነት አይደልም። ኦርቶዶክስ ውስጥ የተዋቀረና ዕምነት ላይ የተቸከለ ሴራ ነው። በገጠር አድባራትና ገዳማት ሳይቀሩ የትጥቅ ትግል ግምጃ ቤትናምሽግ ሆነዋል። ይህቺን ጨዋታ ትህነግና ሻዕቢያ ሲጫወቷት የነበረችና ከዚያው የተቀዳች ናት” የሚሉ ሰዎች ድምጽ የበረከተው። ለዚህ ሲባል ነው “አይንዎትን ለአፈር” ሲብሉ የነበሩትን አባ ማቲያስ ” የምንሰማው እሳቸውን ብቻ ነው” በሚል ውዳሴና ስግደት የተሰጣቸው። “ካድሬ” በሚል በትክክለኛ ስማቸው ሲጠሩ የነበሩት አባ ማትያስ፣ “አባታችን” የተባሉበት ሚስጢር ግልጽ የሆነው ጉዳይ የቀኖናና የእምነት ሳይሆን ሌላ እንደሆነ የትግራይ ኦርቶዶክስ ማፈንገጥን ተከትሎ ” ገደል ይግቡ” የሚል ድምጽ መሰማቱን ተከትሎ ነው። ይህ ደግሞ የሆነው የትግራይ ኦርቶዶስክ መግንጠል ለማራና ኦሮሞ ህዝብ መጋደል አስተዋጾ ስለሌለው ወይም እርባነ ቢስ በመሆኑ ብቻ ነው። ነገ ጠቃሚ ሆኖ ሲገኝ “ጥቁር ልበሱ” እንደሚባል ጥርጥር የለውም። ልብ በሉ የዘመቻውን ፍጥነት፣ የዘመቻውን መናበብ። ቤተክርስቲያን ለምንግስት የሰተችው ቀነ ገደብ። በሁዋላ ጉዳዩ ብቴሌቪሽን ቀርቦ ሲሰማ ጸቡ ሌብነት፣ ገቢ ያለንበት ደብር እኔ ልሾም። ሙስናና ዝርፊያ እንደሆነ በራሳቸው አንደበት ተሰማና ነገሩ “አይይ” አሰንቶ ተዘጋ።

See also  የሱዳኑ ኮርማ ፍፃሜ - ከካርቱም እስከ ካይሮእስሌማን ዓባይ

እዚህ ላይ አስገራሚው ጉዳይ የእምነት ነጻነት የሌለባት፣ ኢየሱስን መጥራት ወንጀል የሆነባት፣ በእምነታቸው ሳቢያ በእስር የሚማቀቁና የሞቱ ዜጎች ባሉባት ኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ተቃጣ ለተባለው ቀውስ ካይሮ ድረስ ወኪል መላካቸው መስማቱ ነው። ኤርትራ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት አማካይነት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ድጋፍ መስጠት ብቻ ሳይሆን ” ከጎናችሁ ነን” ሲሉ መግለጫ አውጥታለች። በርካታ የኤርትራ ነዋሪዎች እስር ቤት እየጮሁ ዝም ያለች ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ መጨነቋን ስትገልጽ ” ነገሩ ሌላ ነው” ሲሉ ጉዳዩ የገባቸው ወዲያው አመልክተዋል።

በሌላ በኩል አሁን አማራ ክልል ያለው እንቅስቃሴ ሌሎች ሃይማኖቶችን የማይቀበል። አንድ እምነት፣ አንድ ቤተክርስቲያን፣ አንድ ጳጳስ የሚል ይዘት ያለው እንደሆነ ራሳቸው ትግሉን የሚመሩት ታጣቂዎች ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋት እየተራባ ነው። ከቆቦ አካባቢ ቅስቀሳው የሃይማኖት እንደሆነ ጠቅሰው በልዩ ሁኔታ እየተነጋገሩ ያሉ መኖራቸውም ተሰምቷል። የዕምነት ጉዳይ የአማራ ጥያቄ እንዳልሆነ እየታወቀ፣ የአማራ ህዝብ እንደ ሌሎች ወገኖቹ ልዩነት ሳይኖረው ከሁሉም እምነት ተከታዮች ጋር እየኖረ ባለበት እንዲህ ያለው አጀንዳ አገሪቱን ለማተራመስ እቅድ የነደፉት አካላት የት ድረስ እንደተጓዙ አመላካች ነው።

” ነገሩ ደስ አይልም። እያስገደዱን ነው። ቅስቀሳው የዕምነት ነው” የሚሉ ምድጾች ተሰምተዋል። ከምንም በላይ ይህን የሚያረጋግጡ መረጃዎች ህዝብ ጆሮ እየገቡ ነው። ኢትዮጵያ የአማራ ናት። አዲስ አበባ የአማራ ናት። አማራ ኦርቶዶክስ ነው። ወለጋ የአማራ ነው። ኦሮሞ ጋት መሬት ኢትዮጵያ ላይ የለውም … የሚሉ መፈክሮች በድምጽ ማጉያ አደባባይ እየተባለ ነው። “ጋላ” በሚል አንድን ታላቅ ህዝብ በአደባባይ ጸያፍ ስድብ እየሰደቡ መፈክር የሚያሰሙት ክፍሎች ምሽጋቸው ኦርቶዶክስ መሆኑንን በነካ አፋቸው ሲገልጹ ቅር የሚላቸው ወገኖች አይኖሩም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው።

ኢሳያስና ኢትዮጵያ

“ኢሳያስ አፉወርቂ የኢትዮጵያ ታሪካዊና ቁልፍ ጠላቷ ነው። ከደርግ ይልቅ እሱን ቀድመን እናስወግደው” በሚል ትህነግ ውስጥ ጥያቄ ያቀርቡና አቋም ይይዙ የነበሩ ከትጥቅ ትግል ጊዜ ጀምሮ ” ነብስ ይማር” እንኳን ሳይባሉ ይወገዳሉ። ኢሳያስ አፉወርቂ ኢሳት በተለይም መሳይ መኮንን በስብከት የኢትዮጵያ ወዳጅና ተቆርቋሪ አደረጋቸው እንጂ አይደሉም። አልነበሩም። ሊሆኑም አይችሉም። “አቅም ካለ እሳቸውን ማስወገድ የኢትዮጵያን መከራ ማሳጠር ነው” የሚሉ ድምጾች የሚሰሙት ለዚህ ነው።

እዚህ ላይብ ትህነግን ኢትዮጵያዊ አድርጎ ለመሳል ሳይሆን፣ ከውስጡ መልካሞችና ሴራው ያልገባቸው እንዳሉ ለማመላከት ብቻ ነው። ሁሉም ሆኖ የራስን ፍርድ ለመፍረድ ኢሳያስ ጸረ ኢትዮጵያ ፈንጂ ካታቀፉ በስተቀር አይተኙም። ለዚህም ብዙ ማስረጃ ማቀርብ ይቻላል።

ቀድመው ትህነግን ፈለፈሉት። እሳቸው ወደ ሻዕቢያ ቁንጮነት ሳይመጡ የተፈጠረ ባይሆንም፣ የትህነግ አላማውና አፈጣጠሩ የሸቢያን ዓላማ ለማስፈጸም እንደሆነ የመጨረሻ ግብሩ ኢትዮጵያን ከአንገቷ ማሳረድና ማስገንጠል መሆኑ በቂ ማስረጃ ነው። ኢሳያስ የሻእቢያ መሪ ከሆኑ በሁዋላ ትህነግን ይበልጥ ያበቁና አብረው ተናበው ኢትዮጵያን ለማዳከምና ለመውጋት እንደተጠቀሙበት አዲስ አበባ ድረስ ሲመጡ እንዴት ተግተልትለው ይጓዙ እንደነበር ማሳያ ነው። አስመራ እንሱ፣ አዲስ አበባ ትህነግ!

See also  «በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!

ከትህነግ ጋር የከርስና የዝርፊያ ጸብ ሲነሳ ኦነግን ማሰልጠን፣ ማስታጠቅ፣ ማጎለበት ጀመሩ። በምስራቅ ለማተራመስ አልሸባብ መርገቻውን ኤርትራ አድርጎ ተራባ። አርበኞች ግንባር፣ ግንቦት ሰባት ሚጢጢም ቢሆን ኤርትራ ከተሙ ተባለ። አንድ ቀበሌ መቆጣጠር የሚችል ሃይል ባይኖራቸውም በፕሮፓጋንዳ ክፍለጦርና ብርጌድ ሆነው ታዩ። የትግራይ ተቃዋሚ ደሚትን መሰረቱ። ለውጡ ሲመጣ ሰላም ወረደ ተባለና ኦነግን በትግራይ ሲለቁት ከፊሉን በጠያራ ኡጋንዳ ዘረገፉ።

ትህነግ የዘወትር ስጋታቸው በመሆኑ መከላከያ ላይ የተፈጸመውን ክህደት ተከትሎ እንዳይሆን አደረጉት። ተዘግቶ የነበረው የኤርትራና ኢትዮጵያ ግንኙነት መከፈቱን ተከትሎ ዶላር አተባውን ኮንትሮባንድ መበራከቱ፣ በኦምሃጀር በኩል የቅባት እህል፣ የእርሻ ውጤቶሽ፣ ክብቶችና ነዳጅ ወደ ኤርትራ በገፍ መግባቱን መከላከያ ሲያስቆም ኩርፊያ ተጀመረ። ትህነግና መንግስት ” ጦርነት በቃ” ሲሉ ኢሳያስ አኮረፉ። ሰላም መስፈኑ ሳይሆን ኢትዮጵያ ምድር ላይ ጦርነት መቆሙ ካላቸው የቆየ አቋም አንጻር አሳሰባቸው፤ ኢትዮጵያ የገነባችው ሰፊ ሃይል ስጋት የሆነባቸው ኢሳያስ ልክ በደርግ ጊዜ እንደሆነው የኢትዮጵያን መከላከያ ለማፍረስ በቂ ልምድ ያላቸውን ሻለቃ ዳዊት አገኙ።

በስጋት ውስጥ ሆነው ጎን ለጎን ግን የአማራ ሃይልን ወዲያው ማስታጠቅና ማደራጀት ጀምረው ስለነበር ከባህር በር አጀንዳ መነሳት ጋር ጎን ለጎን በክረምት እሳቸው ዘንድ የሰለተነው ሃይል ነቅሎ እንዲገባና በሁሉም አቅጣጫ ጦርነት እንዲከፍት ሆነ። በግልጽ የኤርትራው ጄነራል ” ፋኖን እንረዳለን” ሲሉ እንዳስታወቁት አደረጉት።

“ኢሳያስ እያሉ ኢትዮጵያ ሰላም አይኖራትም” የሚሉ ወገኖች፣ “ኢትዮጵያ ከስምንት መቶ ሺህ በላይ የኤርትራ ተወላጆችን አቅፋ ያለ አንዳች ልዩነት እያኖረች እንደዚህ ያለ ደባ የሚፈጸምባት ለምንድን ነው?” ሲሉ ይጠይቃሉ። ኢትዮጵያ ምንም ሳታደርግ ” ጨቋኝ” ተደርጋ በነጻነት ስም የነከሷትን ወገኞች መሸከሟ ሞኝነት ሆኖ በኮንትሮባንድና ዶላር አጠባ መዘረፉ ሳያንስ፣ በሴራ እንድትደምና ይደረጋል። ይህ ንጹህ ህሊና ላላቸው የኤርትራ ተወላጆች ጥሩ የቤት ስራ ይመስለኛል።

ኢሳያስ ባህር ሃይል ሲፈርስ እጃቸው ነበረበት። አሁን ባህር ሃይል ሲቋቋም ደስተኛ አይደሉም። ኢሳያስ አየር ሃይል ሲፈርስ እጃቸው ነበርበት። ዝርፊያ ውስጥም ነበሩ። ብዙ ሃብትም ወስደዋል። ዛሬ አየር ሃይል መቋቋሙና ክንዱን ማፈርተሙ አይስደስታቸውም። መከላከያም ፕሮፌሽናል እየሆነ በስፋትና በጥራት መደራጀቱ እንቅልፍ ነስቷቸዋል። ለሚከተሉት ዳፍንታም ስርዓት እድሜ መርዘም ኢትዮጵያ እንደ አገር መጠንከር የለባትም። እነ መሳይ መኮንን እንደሚሉት ሳይሆን ኢሳያስ ጸረ ኢትዮጵያ መሆናቸውን በየጊዜው ዒትዮጵያ ላይ ከፍለፈሏቸው ጠላቶቿ ቁመናና ባህሪ መረዳት ቀላል ነው።

በሰሜን በተደረገው ጦርነት የዘረፉትንና ያጋጋዙትን መሳሪያና ታንክ እንዲመለሱ መጠየቃቸው ያበሳጫቸው ኢሳያስ ከሻለቃ ዳዊት ጋር አሁን ላይ ዘመቻውን እየመሩት ነው። ላልገባችሁ ጨዋታው ይህን ይመስላል። መከላከያ ላይ አነጣጥሮ ዘመቻ የተጀመረው፣ አዝማሪና ኮማሪቱ ከየጥጉ አዋራውን እያራገፍ በመከላከያ ላይ ጥላቻ እንዲረጭ የሚደረገው እንደ ልማዳቸው ሊያፈርሱት ነው። አውነታው ይህ ነው። ሲሳካ እናደንቃቸዋለን። በነገራችን ላይ የሱዳኑ ጦርነት የዚሁ አካል ነው። እመለስበታለሁ።

የሺጥላ ሃይሉ – አዲስ አበባ – ይህ ጽሁፍ የጸሃፊው አስተያየት ብቻ ነው

Leave a Reply