የህንድ ዋና ከተማ ኒው ደልሂ ከ10 ቀናት በኋላ የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባን ለማስተናገድ ጉባዔው በዝንጀሮዎች እንዳይረበሽ እየተዘጋጀች ነው።
ከተማዋ እንግዶቿን ለመቀበል እያደረገችው ባለው ሽር ጉድ ውስጥ ለአንድ ጉዳይ የተለየ ትኩረት ሰጥታለች፤ ዝንጀሮዎችን ከመሰብሰቢያ አዳራሽ የማራቅ ዘመቻ። በከተማዋ የተለያዩ አቅጣጫዎች አስፈሪ የዝንጀሮ ምስሎች እና ቅርጾችን እያስቀመጠች ሲሆን፥ የእንስሳት ድምጽን የሚያስመስሉ የሰለጠኑ ሰዎችንም ለማሰማራት አቅዳለች ተብሏል።
በኒው ደልሂ ከ20 ሺህ በላይ ዝንጀሮዎች እንዳሉና በየዓመቱ በአማካይ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በዝንጀሮዎች እንደሚነከሱ የታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ዘገባ ያሳያል። “ላንገርስ” የሚሰኙት ጥቁር ፊትና ረጅም ጭራ ያላቸው ዝንጀሮዎች ባህሪያቸው ቁጡ እና ሃይለኛ ናቸው።
በባለሙያዎች ቁጥጥር ካልተደረገባቸውም ጉዳት እንደሚያደርሱ የህንድ የዱር እንስሳት ጥበቃ ተቋም ይገልጻል። እናም ኒው ደልሂ ከፈረንጆቹ መስከረም 8 እስከ 9/ 2023 የምታስተናግደው የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ በዝንጀሮዎች እንዳይታወክ ከ30 በላይ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በየሆቴልና ስብሰባ አዳራሹ ተመድበው ይሰራሉ ተብሏል።
የዝንጀሮዎቹን ድምጽ የሚያስመስሉት ባለሙያዎች ዝንጀሮዎቹ እንግዶቹን እንዳይረብሹ እንደሚያደርጉ ተገልጿል። ዝንጀሮዎቹ ምግብ ፍለጋ ወደ ስብሰባ አዳራሾች እና ሆቴሎች እንዳያንዣብቡም ከተማዋ በየሥፍራው የምግብ ማቅረቢያ እያዘጋጀች ነው ተብሏል።
ኒው ደልሂ በፈረንጆቹ 2014 የላንገርስ ድምጽ የሚያስመስሉና ወደ ፓርላማ እና ሌሎች ቢሮዎች እንዳይገቡ የሚያስፈራሩ 40 ባለሙያዎችን ቀጥራ ነበር። በ2010 የኮመንዌልዝ ጨዋታዎች በከተማዋ ሲደረግም አትሌቶች በእነዚህ ዝንጀሮዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው 38 የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ማሰማራቷን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን ነሃሴ 25/2015
- የበርሊን ማራቶን ባለማዕረግ ትግስት እነ ዱቤ ጂሎ ቢሳተፉ ታዝረከርካቸው ነበርበማራቶን ከሁለት ደቂቃ በላይ ማሻሻል እጅግ የሚደነቅና ያልተለመደ ነው። ባለሙያዎቹ ወይም አሰልጣኞቹ የሮጠችበትን ፍጥነት በሰዓትና ርቀት ከፋፍለው ቢያቀርቡት ምን አልባትም ወንዶችን የሚገዳደር ፍጥነት ተጠቅማ ሮጣለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቴክኒክ ዳይሬክተርና የአትሌቶች ኮሚሽን ሰብሳቢ የነበሩት የዛሬው የተከበሩ ዱቤ ጅሎ አይነቱን ሯጮችን አዝረክርኮ ማሸነፍ የሚያስችላትን ሃይል አሳይታለች። የበርሊና ባለ ማዕረግ ትዕግስት!! ተግስት … Read moreContinue Reading
- የባህር ዳር ነዋሪዎች- ኢትዮጵያን ዜጎች በሁሉም ቦታ እኩል የሚስተናገዱባት ሀገር ማድረግ ይገባልየባህር ዳር ነዋሪዎች የሕዝብን ጥያቄ የመፍታት አቅም፣ ፍላጎት እና ቅንነት ያለው አመራር በመፍጠር ሕዝብን መካስ እንደሚያስፈልግ፣ ኢትዮጵያ በዘር ከመገፋፋት እና ከመጠቃቃት ነጻ የኾነች ፣ዜጎች በሁሉም ቦታ እኩል የሚስተናገዱባት ሀገር እንድትኾን ማድረግና የፌዴራል መንግሥት የአማራ ሕዝብ ኅብረ ብሔራዊ እና ልማት ወዳድ እንጅ ጦርነትን የማይፈልግ መኾኑን በውል በመገንዘብ የሕዝቡን ተዘዋውሮ የመሥራት እና … Read moreContinue Reading
- ለወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ አንድ ሚሊዮን የጉልበት ሰራተኛ ይፈለጋል፤ ከአንድ ነጥን አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሰሊጥ ይጠበቃል“ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል አስተማማኝ ሰላም ያለው እዚህ ነው። ለሰራተኞች እንደ ቤተሰብ ዝግጅት አድርገናል። ኑ” ሲሉ የተሰሙት አምስት መቶና ሶስት መቶ ሄክታር ሰሊጥና ማሽላ ያመረቱ ባለሃብቶች ናቸው። የዞኑ ግብርና ቢሮ ሃላፊ እንዳሉት አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ ኩንታል የሰሊጥ ምርት ስለሚጠበቅ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሰራተኛ ሃይል ያስፈልጋል። የዞኑ አርባ … Read moreContinue Reading
- የጎንደርን ከተማ ምን አይነት ተኩስ እንደሌለ ተገለጸ፤ ጎንደር ተይዛለች ተብሎ ነበር“ጎንደር ከተማን ሙሉ በሙሉ ይዘናታል” ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀው ለጀርመን ድምጽ መረጃ በሰጡ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ቃል አቀባይ አየር ማረፊያውን ሆን ብለው እንዳልያዙ አመልክተዋል። እሳቸው ተናገሩ የተባለው በጀርመን ድምጽ እየተሰማ በለበት ሰዓት በተመሳሳይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ውጊያ መደረጉን ሳያስተባብል ከተማዋን ለመያዝ የገባው ሃይል መደምሰሱን አሃዝ ጠቅሶ አመልክቷል። አገር መከላከያም … Read moreContinue Reading
- “የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ፣ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ”የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ (ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ) የሚለው የቆየ ተረት ልብን የሚያደማ ኩነትን ማሳያ ነው። እቺ መከረኛ ሚስት ባልዋ በእናቷ ልጅ ወንድሟ ተገደለ። ሟች ባል፣ ገዳይ ወንድም … ኢህአፓ “ሃይማኖት ነው” በሚል ሲገልጸው በነበረው ትግል በቀይና ነጭ ሽብር ስም እናቶች የወላድ መካን ሆነዋል። ጧሪ ያጡና ባዶ ቤት ሃዘን … Read moreContinue Reading