የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መታወቂያን በማዘጋጀት እያስፈራራ ሲዘርፍ ነበር በተባለ ተጠርጣሪ ላይ ክስ እንዲመሰረት ተወሰነ

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ተቋም መታወቂያን አስመስሎ በማዘጋጀት ሰዎችን እያስፈራራ ገንዘብ ሲቀበል ነበር በተባለ ተጠርጣሪ ላይ ክስ መመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ።

የክስ መመስረቻ ጊዜ ለዐቃቤ ሕግ የፈቀደው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሲሆን÷ተጠርጣሪው ነስሩ ሳሌ ጀማል ይባላል።

ግለሰቡ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሰራተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ደህንነት ነኝ በማለት ግለሰቦችን በወንጀል እንደሚፈለጉ በመግለፅና መታወቂያውን በማሳየት ከግለሰቦች እስከ 200 ሺህ ብር ጀምሮ ሲቀበል እንደነበር ተመላክቷል፡፡

በዚህም ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት የሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሲከናወንበት መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ በዛሬው ቀጠሮ የምርመራ ስራ ማጠናቀቁንና መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን ለተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አስታውቋል።

የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክተር ዐቃቤ ሕግ ችሎት ቀርቦ የምርመራ መዝገቡን ከፖሊስ መረከቡን ገልጿል። መዝገቡን ተመልክቶም ክስ ለመመስረት እንዲያስችለው የ15 ቀን ክስ መመስረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ተጠርጣሪው በበኩሉ ÷ ከዚህ በፊት ለፖሊስ ተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ መፈቀዱን ጠቅሶ በድጋሚ ለክስ መመስረቻ ተጨማሪ ጊዜ ሊፈቀድ አይገባም በማለት የዋስትና መብቱ እንዲፈቀድለት ጠይቋል።

የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው ችሎቱ ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን ተመልክቶ ክስ ለመመስረት ጊዜ እንደሚያስፈልገው በማመን የተጠርጣሪውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለዐቃቤ ሕግ የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል። ውጤቱን ለመጠባበቅም ለመስከረም 4 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ ፋና


 • ከአራት ወረዳዎች በስተቀር የሽግግር ፍትህ ግብዓቶች ማሰባሰቢያ ውይይት በመላው አገሪቱ ተካሄደ
  “የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጭ ማእቀፎች ዙሪያ በመላዉ አገሪቱ ሲካሄድ የነበረዉ የህዝብ ዉይይት ተጠናቀቀ፤ አራት ወረዳዎች በጸጥታ ምክንያት ውይይቱ አለማከሄዱ ገዝፎ ዜና የሆነበት ዜና በአገሪቱ የሚዲያውን ጨለምተኛነት የሚያሳይ በሽታ ነው” የህግ ባለሙያዎች አስተያየት ሰጥተዋል። በኦሮሚያ ክልል ደምቢ ዶሎና ያቤሎ፣ በአማራ ክልል ሰቆጣና ደብረ ማርቆስ ብቻ ውይይት እንዳልተደረገ ተመልክቷል። ወልቃይትና ሁመራ ምክክር … Read moreContinue Reading
 • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መታወቂያን በማዘጋጀት እያስፈራራ ሲዘርፍ ነበር በተባለ ተጠርጣሪ ላይ ክስ እንዲመሰረት ተወሰነ
  የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ተቋም መታወቂያን አስመስሎ በማዘጋጀት ሰዎችን እያስፈራራ ገንዘብ ሲቀበል ነበር በተባለ ተጠርጣሪ ላይ ክስ መመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ። የክስ መመስረቻ ጊዜ ለዐቃቤ ሕግ የፈቀደው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሲሆን÷ተጠርጣሪው ነስሩ ሳሌ ጀማል ይባላል። ግለሰቡ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሰራተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ደህንነት ነኝ … Read moreContinue Reading
 • በፔንሲዮን የተዘጋው የታሪኩ ህይወት፤ የሚስት ጭካኔ
  ሰዎች በአጋጣሚ ተዋውቀው ትውውቃቸው ወደ ጠበቀ ግንኙነትና ባልንጀርነት ብዙ ጊዜ ያድጋል። በአጋጣሚ የተዋወቁ ሰዎችም በሚኖራቸው ግንኙነት እያደር አንዱ የአንዱን ማንነት፣ ባሕሪ፣ አመለካከት …ወዘተ ይበልጥ እየተረዳ ይሄዳል። በሂደትም ልብ ለልብ ሲግባቡ ወደ ፍቅር ሕይወት ይገባሉ። የፍቅር ሕይወታቸውም አብቦ ሶስት ጉልቻ የቀለሱ ብዙዎች ናቸው። በዚህ መልኩ ከመሰረቱ “ምን አላት? ምን አለው?” በሚል … Read moreContinue Reading
 • የቡና ግብይትና ጥራት ቁጥጥር ሕግ (ክፍል አንድ)
  አረንጓዴ ወርቅ የሚል ስያሜ የተሰጠው እና የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ የጀርባ አጥንት የሆነው የቡና ምርት ሻጭ እና ገዢ የሚገናኙበት ሂደት እና አሰራር ሕግን ያልተከተለ በመሆኑ፤ የዓመታት ልፋታቸውን ያክል ገቢ ማግኘት ያልቻሉ አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች የቅሬታ ምንጭ ሲሆን ይስተዋላል። ሕገ-ወጥ የቡና ግብይትን ለማስቀረት፣ የቡና አመራረት ስታንዳርዱን የጠበቀ ለማድረግና ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት … Read moreContinue Reading
 • የአክሲዮን ማኀበር እና የኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ልዩነት
  1/ #አክሲዮን ማህበር የአክሲዮን ማህበር ማለት ዋናው ገንዘቡ ወይም ካፒታሉ አስቀድሞ ተወስኖ በአክሲዮን የተከፋፈለና ለዕዳው ንብረቱ ብቻ ዋስ የሆነ ማህበር ነው፡፡ ይህም ማለት አባላት አስቀድሞ ተወስኖ የተከፋፈለ አክሲዮን በመግዛት የንግድ ማህበሩ ባለቤት የሚሆኑበት ሲሆን ማህበሩ በሚያጋጥመው ማናቸውም አይነት አዳ እያንዳንዱ አባል ኃላፊነት ሊወስድ የሚችለው በማህበሩ ላይ ባለው ካፒታል መጠን ብቻ … Read moreContinue Reading
See also  "የፌደራል ፖሊስ አባላት ነን"በማለት ወንጀል የፈፀሙ በቁጥጥር ስር ዋሉ

Leave a Reply