በ60 ዓመቱ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመዉ ግለሰብ የእድሜውን አመሻሸ ማረሚያ ቤት አድርጓል፡፡

ተከሳሽ ያሲን ባሙድ ኢብራሂም ይባላል የ60 አመት እድሜ ያለዉ ግለሰብ ሲሆን የ9 አመት ህጻን ልጅን አስገድዶ በመድፈሩ ምክንያት በፈፀመው በህፃናት ልጆች ላይ በሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበትና የክስ ሂደቱ ሲካሄድ ቆይቶ ወንጀለኛ መሆኑ በመረጋገጡ በእስራት ተቀጥቷል፡፡

የዐቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር እንደሚያስረዳዉ ወንጀለኛው ከእርሱ ጋር ተቃራኒ ፃታ ካላትና ዕድሜዋ 13 አመት ካልሞላት ልጅ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ለመፈፀም አስቦ ከ2007 ዓ.ም ነሐሴ ወር ጀምሮ ባሉት የተለያዩ ቀናት በተደጋጋሚ አስገድዶ ደፍሯታል፡፡

በበመጨረሻም በቀን 6/10/2011 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 7፡30 ስአት ሲሆን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታዉ ዲ አፍሪካ እየተባለ ከሚጠራዉ አካባቢ ከሚገኝ የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ውስጥ የግል ተበዳይን አስገድዶ የደፈራት በመሆኑ በዐቃ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ከሳሽ የፌዴራል ዐቃቤ ህግ 4 የሰዉ ምስክሮችንና የሰነድ የህክምና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ለፍረድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በቀን 20/7/2013 ዓ.ም ባስቻለዉ ችሎት ተከሳሽን ወንጀለኛ ነህ ሲል የቅጣት ዉሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን ወንጀለኛዉ የቤተሰብ አስተዳደሪ ና ታሚሚ መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት ይዞለት በ13 ዓመት ፅኑ እስራት እንቀጣ ወስኖበታል፡፡

Via attorney general

Categories: law

Tagged as:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s