ቀደም ሲል መንግስት እያለ የአሜሪካ መንግስት ከሽብረተኞች መዝገብ ውስጥ ያልፋቀውና በቅርቡ ፓርላማ ከኦነግ ሸኔ ጋር አሸባሪ ብሎ የሰየመው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ፣ ሃያ ሁለት ዓላማውን የማይቀበሉ የአመራር አባላትን መግደሉና ሃያ ያሚሆኑትን ማገርቱ ተገለጸ።
“የተበተኑ የአሸባሪው የሕወሓት ርዝራዦች እስከ አሁን 22 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን ገድለዋል፤ 20 የሚሆኑትን አግተዋል” ሲል ያስታወቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ነው።
የተበተኑ የአሸባሪው የሕወሓት ርዝራዦች በተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች እስከ አሁን ድረስ ብቻ 22 የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር አባላት መግደላቸውን ፣ ከዚህ በተጨማሪ 20 የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላት መታገታቸውን እና 4 የአስተዳደሩ አባላት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ሆስፒታል መግባታቸውን ስፍራና የስራ ሃላፊነት ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።
“እየታገልኩ ያለሁት ለትግራይ ህዝብ ነው የሚለው አሸባሪው ሕወሓት ይልቁንም የክልሉን ሃብት እያወደመ እንዲሁም በክልሉ መረጋጋትን ለማምጣት የሚሰሩ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላትን እየገደለና እያገተ” ነው ሲል መረጃው አስታውቋል።
በትግራይ የሰብአዊ ዕርዳታ በወጉ እንዳይዳረስና በነጻነት እንዳይሰራጭ ህወሃት በየስርቻው እየተሹለከለከ እክል መፍጠሩን፣ ሰላማዊ ዓላማውን የማይደግፉትን አካላት መግደሉን በመጥቀስ የክልሉ ምክትል አስተዳዳሪ መናገራቸው ይታወሳል። ህወሃት ይህን ቢያደርግም የውጭ ሚዲያዎችና የመብት ተቆርቋሪዎች መረጃውን አይጠቀመኡበትም።
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ።… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል