በትውልድ ሱዳን በዜግነት እንግሊዛዊ፣ በእንግሊዝ የሲኤንኤን ሪፖርተር ኒማ አልባጊር ክፍል ሁለት ተውኔቷን ያካሄደቸው በዋነናት ሳማንታ ፓወር፣ ሊንዳ ቶማስና ማርክ ሎውኮክን በመያዝ ከአፍሪካና አውሮፓ ኮሚሽን ለዓይነት የተካተቱበት ቡድን በመያዝ የአውሮፓ አሜሪካ የጠረጴዛ ውይይት ለአስቸኳይ እርዳታ በሚል ነበር።
ኒማ እንደ ፊልም አክተር “ ጋዜጠኞች ነን፣ ፈቃድ አለን…” እያለች ዋሻ ዋሻውን ስትዞርና በመወራጨት ከመከላከያ አባላት ጋር የነበራትን ግንኙነት በፊልም እያሳየች በአክሱም ተፈጸመ ያለችውን የዘጠኝ ደቂቃ ትረካ አቅርባ ነበር። በዘገባው የኤርትራ ወታደሮችን ናቸው ያለቻቸውን አሳይታለች። ነገር ግን መንግስት ፈቅዶላት ያነጋገረቻቸውን በሙሉ ድምጻቸውን በመዋጥ ሙያዊ ውሏን የበጠሰች፣ ምግባረ ብልሹና አድረገው ፈርጀዋታል።
READ ALSO THIS የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች
“ሁለት ጉዳዮች ወለል ብለው ይታያሉ” ዋሲሁን ሰማን። ጋዜጠኛዋ መሰረቷ ከሱዳን ነው። የምትኖረውና የተማረችው እንግሊዝ ነው። እነዚህ ሁለት ጉዳዮች አያይዞ ለሚያየው የኒማ ኢልባጊር ዘገባ መነሻና መድረሻ ይገባዋል። ይህ ሊደበቅ የማይችል ጉዳይ ነው። ሲታሰርና ሲፈታ ከነበረው ጋዜጠኛ Continue Reading
ይህቺ ሱዳናዊት ሳማንታ ፓወር፣ ሊንዳ ቶማስና ማርክ ሎውኮክን ከፊት አሰልፋ ” በአስቸኳይ እርዳታ” ስም ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ ስታካሂድ ዋናው ዓላማ በቀጣይ የጂሰባት አገሮች ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያን አንገቷን የሚቀነጥስ ውሳኔ እነዲወሰን ጫና ላምሳደር ነበር። የሆነው ግን የተገላቢጦሽ ነው። አቶ ጥበቡ እንዳሉት ኢትዮጵያ ክፉውን ጊዜ ያለፈች ይመስላል።
የዘወትር ተባባሪያችን የአውሮፓው ዲፕሎማት እንዳሉት ” ዲፕሎማሲው ላይ በጥብቅ እየተሰራ ነው። ሁሉም ጉዳይ መልክ ይይዛል” ሲሉ የጂ ሰባት አገሮችን ውሳኔ ለስላሳና የሴራው አምራቾች ከጠበቁት በታች የሆነ እንደሆነ አመልክተዋል። ግን ደረት አያስነፋም።
READ ALSO THIS የG-7 ሀገራት መግለጫ ስለኢትዮጵያ ምን አለ?
በእንግሊዝ እየተካሄደ ያለው የቡድን 7 ሃገራት ስብስባ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል:: በመግለጫው የኢትዮጵያ ጉዳይም ተካቷል:: በአንቀፅ 54 ላይ የሰፈረው መግለጭ ቃል በቃል የሚከተለውን ይላል። ትርጉም 54. “በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ባለው ግጭት እና እየወጡ ባሉ ሪፖርቶች ምናልባት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ሁኔታ ውስጥ ሊሆኑ ስለሚችሉ የሰብአዊ አደጋዎች በጣም ያሳስበናል፡፡ የጾታ ጥቃትን ጨምሮ እየተፈፀሙ ያሉContinue Reading
በስብሰባው ላይ ጫና ለማሳደር ሚዲያዎች ያራገቡትን የሴራ ዘመቻ ለመመከት ከአውሮፓ አገራትና ቁልፍ ወዳጅ ከሆኑ ክፍሎች ጋር ሰፊ ውይይት፣ መካሄዱን መንግስትም ይፋ እንዳደረገው ባልስልጣናቱ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን መልዕክት በመያዝ ባካሄዱት የፊት ለፊት ንግግር ከፍተኛ ለውጥ መታየቱን ዲፕሎማቱ አስታውቀዋል። ከሁሉም በላይ ግን ኢትዮጵያዊያን የፈጠሩት አንድነትና ያለመታከት ያካሄዱት ዘመቻ ታላቅ ክብር የሚሰጠው እንደሆነ ገልጸዋል።
አቶ ጥበቡ ለኢትዮ 12 በላኩት መልዕክት “በቃ ይሄው ነው። ማለት ያለባቸውን ብለዋል። ያሉት ሁሉ ከቀድሞው የለዘበ እና ከተጠበቀው አንፃር ኢምንት ነው” ብለዋል። የአማራ ሚሊሻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ወዘተ የሚሉ አልስፈለጊ ጉዳዮችን ጭራሽ አለማንሳታቸው በዛኛው ጎራ ለቆሙት ሽንፈት እንደሆነ ጠቅሰዋል።
” ማዕቀብም ሆነ ማስጠንቀቂያ የለውም።ያሳስበናል ያሉትን ሃሳብ ነው ያቀረቡት።ያወገዝነውን ነው ያወገዙት። መፍትሄ ያሉትን ጥሪ ነው አቅርበዋል” ያሉት አቶ ጥበቡ፣ ለዚህም ቢሆን መንግስት የተደራጀና አጥጋቢ ምላሽ መስጠት ብቻ እንደሚጠበቅበት ነው ያመለከቱት።
እንደ ዲፕሎማቱ ሁሉ አቶ ጥበቡም ዲፕሎማሲው ላይ በጥብቅ ከተሰራ ሁሉም ነገር የሚለወጥ ስለመሆኑ የጂ ሰባት አገሮች የአሁኑ ውሳኔ ምልክት እንደሆነ ገልጸዋል። መልዕታቸውን ሲያተቃልሉም “ክፉው ጊዜ በእርግጥም አልፏል፤ ዛሬ የኢትዮጵያ ልጆች ከሰሞኑ ጭንቀት እፎይ ብለዋል፤ መንግስት ይህን እድል ይጠቀምበት፤እስከ መጨረሻው ሁኔታውን ይቀይረው፤ ኢትዮጵያዊያንም ህብረታችንን እናጠናክር” ብለዋል።
.
በሌላ በኩል የሚሰጡ ጥቅል አስተያየቶች “በጠላትነት የያዙን የዩኤስአይዲ ሳማንታ ፓወር፣ ሊንዳ ቶማስ ፣ እንግሊዛዊው የተባበሩት መንግስታታ የሰብአዊ እርዳታ ዘርፍ ሃላፊ እንግሊዛዊ ሰር ማርክ ሎውኮክ ሃዘን ተቀምጠዋል” የሚሉ አስተያቶች እየተሰሙ ነው። አንዳንዶች ደግም “እነ ማርቲን ፕላውት ቴድሮስ አድሃኖም እና ሌሎቹ ቡድንተኞች በሙሉ ልባቸው ወድቋል” ብለዋል። ሁሉም የጠበቁት ስላልሆነላቸው “ጥልቅ ሃዘን ላይ ናቸው” ሲሉም የሳፉ አሉ።
ሰሞኑን ሳማንታ ፓወር እና ሊንዳ ቶማስ ተራ አክቲቪስት ሆነው Tigrai can’t wait ማለት ሁሉ ጀምረው እንደ ነበር ያወሱ ” ኢትዮጵያ ተረፈች” ሲሉ አፊዘውባቸዋል። ከመግለጫው በኃላ ግን ሳማንታ ፓወር የትግራይን ጉዳይ ትታ ስለ ሆንድራንስ ስለ ጓቲማላ ስለ ኤልሳልቫዶር መፃፍ መጀመራቸውን ጠቅሰው ያሽሟተጡም አሉ።
“የኢትዮጵያ ጠላቶች ልባቸው ወደቀ” ብል ጀምሮ “የጁንታው የቱዊተር ታጋዬችም ረሃብ ማለት እንዳላዋጣቸው ስላወቁ ማርቲን ፕላውት የጀመረውን ዘመቻ “ኢትዮጵያ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ወደ ትግራይ አጓጉዛለች በማለት ከበሮ እየመቱ ነው” ያለው ሳለሁልህ አየለ ነው። ሳሳሁልህ “ገንዘባቸውን በሎቢስት እየጨረሱ ስለሆነ እኛም፣ ኢትዮጵያም፣ የትግራይ ሕዝብም በቅርቡ ያርፋል። ምክንያቱም ተስፋቸው በቡድን ሰባት ሃገራት መግለጫ አርቀው ቀብረውታልና! በኢትዮጵያ ስም ተሹሞ ኢትዮጵያን እያረደ ያለው ቴዎድሮስ አድሃኖምም መጽናናት ይሁንለት” ሲል አስተያየቱን ያጠቃልላል።
በጂ ሰባት አገራት ውሳኔ ኢትዮጵያ የማትስማማበት ጉዳይ አንድና አንድ ብቻ ነው። እሱም ከትህነግ ትርፍራፊ ሃይል ጋር መደራደር። ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከፍተኛ የሎቢ ስራ መሰራቱን በመጥቀስ ከፍተና ድል እንደሚመዘገብ በስራቸው ላሉ መናገራቸውን አካታን ረሃብን የትግል መሳሪያ በማድረግ የተካነው ትህነግ ድርድርን በረሃብ ጫና ለማምጣት እየሰራ ያለውን ሪፖርት እናቀርባለን።
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል