ዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት የመጀመሪያው ምዕራፍ በስኬት መጠናቀቁን መንግስት አሰታወቀ

  • ጠላት በቀጣይ ዘመቻ ለኢትዮጵያ ስጋት እንዳይሆን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚውሰድበት አስታውቀዋል።
  • ዘመቻ ለህብረ ብሄራዊ አንድነት በድል በመጠናቀቁ የመከላከያ ሰራዊት ለጊዜው ባለበት ስፍራ ረግቶ እንዲቆይ ከመንግስት ትዕዛዝ ተላለፈ።
  • የዋግ ኅምራ አካባቢዎች ነጻ በማውጣት የዞኑን ዋና ከተማ ሰቆጣን ተቆጣጥረዋል፡፡

ዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት ወራሪውን ሀይል ከአማራና ከአፋር ክልሎች በማስወጣት በኢትዮጵያዊያን አሸናፊነት ተጠናቅቋል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት የመጀመሪያው ምዕራፍ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ዘመቻው ዓላማውን አሳክቶ በድል መጠናቀቁን የገለጹት ሚኒስትሩ የሽብር ቡድኑን ከአማራና ከአፋር ክልል ደምስሶ በማስወጣት ሂደት ታላቅ ጀብድ እንደተፈጸመ ጠቅሰዋል።

ጠላት የመሻትትና የማድረግ አቅሙ የተዳከመ ሲሆን፤ በቀጣይም ለኢትዮጵያ ስጋት እንዳይሆን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚውሰድበት አስታውቀዋል።

ለውጤቱ የመላው ኢትዮጵያውያን ተሳትፎም ከፍተኛ እንደነበር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።


– ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች የሰቆጣ ከተማን ተቆጣጣሩ፤

በአንጸባራቂ ድል ወደፊት እየገሠገሡ የሚገኙት ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ የጸጥታ ኃይሎች አብዛኞቹን የዋግ ኅምራ አካባቢዎች ነጻ በማውጣት የዞኑን ዋና ከተማ ሰቆጣን ተቆጣጥረዋል፡፡

አካባቢው ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በሚወጣበት ጊዜ የዋግ ኅምራ ሚሊሻዎች አስደናቂ ጀብዱ የፈጸሙ ሲሆን፣ የአካባቢው ሕዝብም ከመከላከያ ሠራዊትና ከአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመጣመር ደጀንነቱን በብቃት አሳይቷል፡፡ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ የጸጥታ ኃይሎች ቀሪዎቹን ሥፍራ እያጸዱ፣ የፈረጠጠውን የአሸባሪውን ጀሌ እየደመሰሱ፣ ወደ አበርገሌ በመገሥገሥ ላይ ይገኛሉ፡፡
በተያያዘም ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች፣ በቆቦ ግንባር በአንድ በኩል ዋጃና ጥሙጋ ላይ የሠፈረውን የጠላት ኃይል በመጥረግ ወደ አላማጣ ከተማ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተኩለሽን ተቆጣጥረው በማጽዳት፣ ወደ መረዋና ኮረም እየገሠገሡ ይገኛሉ፡፡

በእሳታማው የጀግኖች ክንድ የተደቆሰው አሸባሪው ሕወሐት፣ ተቸካይና ኋላ ቀር በሆነ የጦር ዘይቤ፣ ዕብሪትን እንደ መሣሪያ በመጠቀም፣ ከገባባቸው የአማራና የአፋር ክልል አካባቢዎች እንደገባ መውጣት አቅቶት፣ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሣራ ደርሶበት ተደመስሷል፡፡ ይሄንን ሐፍረቱን መሸፈን ሲያቅተው በአንድ በኩል ለሰላም ሲል የወጣ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሽንፈቱ ውኃ የማይቋጥር ምክንያት እያቀረበ፣ አድኑኝ የሚል እሪታ እያሰማ፣ በለመደው ውሸት የትግራይን ሕዝብና የዓለምን ማኅበረሰብ ለማደናገር እየሞከረ ይገኛል፡፡


በዚህ ጦርነት የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ የሆነውና አሸባሪውን ሕወሐት በጀግንነት የታገለው የዋግ ኅምራ ሕዝብ፣ በጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ የጸጥታ ኃይሎች፣ እንዲሁም በራሱ በዋግ ኅምራ ሕዝብ ትግል፣ ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በመውጣቱ፣ በዚሁ አጋጣሚ መንግሥት እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት ይወዳል፡፡
ነጻነታችንን የምናስከብረው በተባበረው ክንዳችን ነው!
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Leave a Reply