ቻይና አስጠነነቀች !!!!

ይኸ ጽሑፍ ሰፊ ነው። በምክንያት ነው። ዝለቀው።

ቻይና የትኛውም የአለም አገር ሩሲያን በሚመለከት ሁለት ቃላትን እንዳይጠቀም አስጠነቀቀች። እነሱም ወረራ (invasion ) እና hack ( የሳይበር ጥቃት ) የሚሉት ናቸው።
(ወንድወሰን ሰይፉ ቅድስ )

እንደ ቻይና ሩሲያ እያካሄደች ያለችው ወታደራዊ ኦፕሬሽን እንጂ ወረራ አይደለም። ይተዋወቃሉ – ኢትዬጵያዊዉ ቅን ወገኔ !!!

አየህ !!! ሶቪየት ሕብረትን ለማፈራረስ የ CIA እና የእንግሊዝ ደህንነት ሚና ከፍተኛ ነበር። ሶቪየት ከተበተነች በኋላም አገራቱ በሰላም እንዳይኖሩ Revolution of Identity (የማንነት አብዬት ) የሚለውን ያቀበሏቸው እነሱ ናቸው።

እናምልህ የስልጣን ስግብግቡ ሴረኛ ጭፍራም ይኸንን መሰሪ ፎርሙላ ተቀበላቸውና ተጠቀመው ። ይኸም በአንድ አገር ለረጅም ዘመን ሲኖሩ ተጋብተውና ተዋልደው ፥ በታሪክና በደም ተሳስረው ተቀላቅለው በሚኖሩት የአንድ አገር ሕዝቦች መካከል እሳት ለኮሰ።

አዘርባጃን ውስጥ የነበሩ አርመኖች ከአዘርባጃን ውጡ ተባሉ። አርመኒያ ውስጥ የነበሩ አዘርባጃኖች ከአርመኒያ ውጡ ተባሉ። ……………………………

ዩክሬን ውስጥ የፓለቲካ ስልጣን ለይ የነበሩ ሩሲያውያንም ከያሉበት ተባረሩ። በየአገራቱ የተገፉት እነዚህ ማይኖርቲዎችም ነፍጥ አነሱ።……….

የሐይማኖት አጀንዳ ፈንጂ ፈነዳዳ። ከዚያ በፊት እንደ አንድ አገር ሲኖሩ ያልነበሩ አዳዲስ የድንበርና መሰል የግጭት አጀንዳዎች ፈነዳድ። ………………………

ዛሬ በሩሲያና በዩክሬን እንደምታየው ሁሉ ቀድሞ የአንድ አገር ዜጎች በነበሩ አዲሶቹ አገራት መካከል ሰላምና መረጋጋት የለም። ……………..

ይኸን የሚያውቁት ፑቲንና ሩሲያውያን ታዲያ ምእራባውያኑና አሜሪካ ዩክሬን ለይ የተሰባሰቡበት የሚቀብሩት ጸረ ሩሲያና የምስራቅ አውሮፓ ፈንጂ አለ ብለው አመኑ።

ይኸን በረቀቀው የኬጂብ የስለላ መነጽር አረጋገጡ። እንደምታየው የሩሲያ ወታደሮች የሞት የሽረት ትግል አድርገው ትናንት ግማሽ አዲስ አበባን በሚያህል ቦታ የኒውክለር ፕላኔቴሽን በሚስጥር የሚመረትበትን ቦታ ተቆጣጠሩ።

ይኸ ቦታ ከዚህ በፊት የሶቪየት የአቶሚክ ቦምብ ማጉለያ ግዙፍ ጣቢያ የሚገኘበት ሲሆን በአንድ ወቅት ከኒውክለር ጣቢያው ሳይታሰብ ባፈተለከ የኒውክለር ጨረር በርካቶች የተቀበሩበትና እስከዛሬም በካንሰር የሚሰቃዩበት ነው።

እዚህ ቦታ የሚዘጋጀው የኒውክለር ፕላንቴሽን ለበጎ አላማ ሀይል ለማመንጨት ከመሰለህ ከኢትዬጵያዊ ቅን ፍርድ ሕመምህ አልተፈወስክም ማለት ነው።

ራሳቸው የዩክሬኑ መሪ ሙኒክ ለይ እንዳሉት የዩክሬን ደህንነት ኒውክለር በመታጠቅ ለይ የተመሰረተ ነው ከማለታቸው ስትነሳ በቦታው ይዘጋጅ የነበረው የኒውክለር ፕላንቴሽን አላማ ይገባሀል።

እና ዩክሬንስ አገር አይደለችም ወይ ብታደርግስ ምናለበት የሚል የቅን ተፈጥሮህን ጥያቄም ትጠይቅ ይሆናል።

አየህ !!! ሶቪየት እንድትፈርስ ከፈረሰች በኋላ እንደገና እንድትፈርስ ያሸመቀው ሀይል ይኸንና መሰል የወታደራዊ የደህንነት ጣቢያዎችን ከመቶ በላይ በሆኑ የሚስጥር ስፍራዎች የሚያደራጅና የሚያስታጥቀው ለዩክሬንም ለምስራቅ አውሮፓም ብሎ አይደለም።

የሚፈራትን ሩሲያን ለማጥመድ የሚጠቀምበት ስትራቴጂያዊ ማጥቂያው ነወ ብለህ ለማሰብ ግን በእርግጥ ራስህን ካለህበት አጥር አውጥተህ በዚያ አካባቢ ጭብጥ ውስጥ ማሴገባት የግድ ይኖርብሀል። ያለዚያ አይገባህም።

እኔ እንዲህ ቦርቀቅ አድርጌ የማወራህ በአገርህ ለይ የተጠመደውን ሴራ በዚህ አይን እያየህ እንዲገባህም ጭምር ነው ወገኔ !!!

ታዲያ ለዚህ ነው ይኸን ሚስጥር የሚያውቁት ቻይናዎች በዚህ የሩሲያ ምእራባውያን ጦርነት ለይ በሩሲያ ለይ ወረራ የሚል ቃል አትጠቀሙ ለማለት የደፈሩት።

ቻይናዎች ይኸን ያሉት ግን በምክር ሳይሆን በማስጠንቀቂያ ቶን ነው። ለምን ?! ሀከርም የሚል ቃል ሩሲያ ለይ አትጠቀሙ በማለትስ ያስጠነቀቁት ለምንድ ነው ?!

የገዘፈ እውነተኛ ሚስጥር አለ። ቀጥለን እናወራለን።

(ወንድወሰን ሰይፉ ቅድስ )

Leave a Reply