ኢትዮጵያ ወርቅ እንዳትሸጥ ዘመቻ ተጀምሯል፤ ኢትዮጵያዊያን ለእርስ በርስ ሽኩቻ ትኩረት ሰጥተዋል

ኢትዮጵያ ወርቋን ግጭት ካለባቸው ዞኖች እንደምታወጣ በማስመስል የተጀመረውን ዘመቻ በስውር ከሚመሩት መካከል አንዱና ዋና ነዋሪነታቸው እዛው ሲውዘርላንድ የሆነ የትህነግ ግንባር ቀደም አባል እንደሆኑ፣ ለጊዜው በስም መጥቀስ አስፈላጊ ባይሆንም ህዝብ እንደሚያውቃቸው የዜናው ባለቤት ለኢትዮ 12 ነገረዋል።

ኢትዮ 12 ዜና – ኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ቢሰፍንባት ከፍተኛ ሃብት የምታገኘው ከወርቅ እንደሆነ በዘርፉ የተሰማሩ ይገልጻሉ። በአገሪቱ በተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅ ቢኖርም በሙሉ ሃይል ጥቅም ላይ ማዋል አልተቻለም። አሁን ላይ የማዕድን ዘርፉን ለማንቀሳቀስ ቢታሰብም የሰላሙ ጉዳይ እንቅፋት መሆኑ ሳያንስ አዲስ ዘመቻ መጀመሩን ኢትዮ 12 ሰምታለች።

እንደ መረጃው ኢትዮጵያ በያዝነው የበጀት ዓመት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያገኘችበት የወርቅ ሃብቷን በአብዛኛው የምትገዛት ሲውዘርላንድ ግዢ እንድታቆም ከፍተኛ የውስወሳ ስራ ተጀምሯል። የትህነግ ደጋፊና ስትራቴጂክ አጋር የሆኑ ኢትዮጵያ የምትልከው ወርቅ ከጦርነት ቀጠና የሚወጣና ገቢውም ጦርነቱን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ በማስመሰል ነው የውስወሳ ስራው እየተሰራ ያለው።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ወርቅ የምትልከው ከትግራይ አካባቢ የሚገኘውን ሳይሆን ከሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች መሆኑ እየታወቀ ይህ መሰሉ ዘመቻ መካሄዱ ያስገረማቸው የመረጃው ባለቤት ” መንግስት መረጃው አለው። አስቀድሞ እየሰራበት ነው። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያዊያን ለእርስ በርስ ሽኩቻ ቅድሚያ መስጠታቸው ከዘመቻው በላይ የሚደንቅ ነው” ብለዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች የወርቅ ኤክስፖርት እጅግ ካሽቆለቆለበት አገግሞ ባለፉት አራት ወራት 3 ሺህ 602 ኪሎ ግራም ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ 265 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ እንዳሳገኘ ከወር በፊት ሪፖርት መደረጉ ይታወሳል።

በእቅድነት የተያዘው የወርቅ ምርት የተከለሰ ሲሆን፣ በተሻለ መንገድ ኢኮኖሚውን መደገፍ በሚያስችል መልኩ ምርቱን ለመጨመር ከክልል አመራሮቹ ጋር መግባባት ላይ መደረሱንም ማዕድን ሚኒስቴው አስታውቆ እየሰራ ሲሆን፣ በቀጣይም ዘርፉን ዘመናዊ መልክ ለማስያዝ ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የማዕድን ላቦራቶሪና ምንጠሪያ ለመግንባት በስራ ላይ መሆኑ ተጠቁሞ ነበር።

በዚሁ መነሻ በምዕራብ ወለጋና ሜድሮክ አዲስ ባገኘው ሳካሮ፣ በትግራይ ኢዛና፣ እና በቤኒሻንጉል ያለውን ከፍተኛ ሃብት ለመጠቀም እየተሰራ ባለበት ወቅት ላይ ሲውዘርላንድ ወርቅ እንዳትገዛ የውስወሳ ስራውን የሚሰሩት ተከፋይ ደላሎች ምን ያህል ይሳካላቸዋል? ለሚለው የመረጃው በላቤት ” አማራጭ ገባያ ማፈላለግ፣ ሲውዘርላንድ የተሳሳተ ውሳኔ ውስጥ እንዳትወድቅ ቅስቀሳውን ማምከን ይገባል” ብለዋል።

See also  "የምንዛሬ ለውጥ ሊደረግ ነው በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሁሉ ሀሰት ነው " አቶ ማሞ ምህረቱ

በተባበሩት መንግስታትም ሆን በአውሮፓ ህብረት ደረጃ ኢትዮጵያን ለማዕቀብ የሚጥል አንዳች ጉዳይ እንደሌለ የገለጹት የዜናው ባለቤት” ኢትዮጵያ ለዜጎቿ መድሃኒት፣ ምግብ፣ ነዳጅና የመሳሰሉትን ቁሳቁሶች የምትገዛ አገር መሆኗን ገዢዎቹ ቢያውቁም መንግስት በጀመረው የዲፕሎማሲ ስራ ሊገፋበትና የትህነግ ደጋፊዎች ሃብታቸውን ተጠቅመው ሊያሳድሩ የሚችሉትን ጫና ከወዲሁ በመለየት ሊያከሽፍ ይገባል” ብለዋል።

የኢትዮ12 የቅርብ የመረጃ አጋር የሆኑት ዲፕሎማት ” መንግስት በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እያለ ዜጎች አገራቸውን የዘነጉና ሌላ አማራጭ ያላቸው ይመስል በውስጥ ሽኩቻ ላይ መጠመዳቸው አሳዛኝና አስገራሚ ነው። ሌሎች ለክፉ ተግባር ይህን ያህል መንገድ ርቀው ሲሄዱ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ደረጃ የእርስ በርስ ትንቅንቅ ውስጥ መግባታቸው ልክ እንዳልሆነ፣ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በዚህ ላይ ቢያተኩሩ ይሻላል” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ወርቋን ግጭት ካለባቸው ዞኖች እንደምታወጣ በማስመስል የተጀመረውን ዘመቻ በስውር ከሚመሩት መካከል አንዱና ዋና ነዋሪነታቸው እዛው ሲውዘርላንድ የሆነ የትህነግ ግንባር ቀደም አባል እንደሆኑ፣ ለጊዜው በስም መጥቀስ አስፈላጊ ባይሆንም ህዝብ እንደሚያውቃቸው የዜናው ባለቤት ለኢትዮ 12 ነገረዋል።

ኢትዮጵያ በባህላዊ መንገድ ከፍተኛ ወርቅ እንደምታመርት ይታወቃል።

ፎቶ – አሶሳ ወቅ ፕሮጀክት

Leave a Reply