በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ጨረታ ያሸነፈው “ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ” የስራ ፈቃድ አገኘ።በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ያገኘው ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ የተባለው ኩባንያ ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።
የስምምነት ፊርማው የተከናወነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የኬኒያው ፕሬዝዳነት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት ነው።የኢትዮጵያ ኮሙንኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ፤ ከቮዳኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ሻሚል ጆሱ፣ ከሳሪ ኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ኢድግዋ እንዲሁም ከሲሚቶሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ስምምነቱን ተፈራርመዋል።ኩባንያው ጫረታውን ያሸነፈበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን የኢትዮጵያ ከሚዩኒኬሽን ባለስልጣን መግለፁ ይታወቃል።
በዛሬው እለት ደግሞ ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችለውን ፈቃድ ያገኘበት መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል።ግሎባል ፓርትነር ፎር ኢትዮጵያ የኬኒያው ሳፋሪ ኮም፣ የዩናይትድ ኪንግደም ቮዳፎንና ሲዲሲ ግሩፕ፣ የደቡብ አፍሪካውን ቮዳኮም የጃፓኑን ሲሚቶምና ዲኤፍሲን በጥምረት የያዘ ኩባንያ ነው።ኩባንያው በቀጣይ አስር ዓመታት ከ8 ቢሊዮን
ዶላር በላይ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።በዚህም ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላ ዜና የጃፓኑ ሱምቶም ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ በቴሌኮም ዘርፍ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ገለጸ በቴሌኮም ዘርፍ የውጭ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ መንግስት በወሰደው ውሳኔ መሠረት ጨረታውን ያሸነፈው ‘የግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ ‘ ድርጅት አንዱ የሆነው የጃፓኑ ሱምቶም፤ በቀጣይ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ከሁለት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡
የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ቶሽካዙ ናምቡ የኢንቨስትመንት ዕቅዳቸውን ያስታወቁት፤ በጃፓን የኢ.ፌ.ዲ.ረ አምባሳደር ካሣ ተክለብርሃን ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው። ምክትል ሥራ አስፈጻሚው ኮርፖሬሽናቸው ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የኢትዮጵያ መንግስት በግልጸኝነት ባካሄደው የጨረታ ሂደት በማሸነፋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡አምባሳደር ካሣ ተክለብረሃን በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በጃፓን፣በኤሽያ እና በአፍሪካ ያለው የካበተ ልምድ በኢትዮጵያ ኢንቬስት በማድረግ እንዲደግመው ጥሪ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል።
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ ሺህ በላይ ማሻቀቡ ይፋ እየሆነ ባለበት ወቅት ነው። መንግስት ሰላማዊ ዜጎችን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት አግባብ እንዳልሆነ ጠቅሶ ” መንግስታዊ ሃላፊነትን መወጣት ፍርሃት አይደለም” ቢልም የትግራይ አመራሮች ሂደቱ ከመንግስት ጋር በተደረገ ስምምነት እየተከናወነ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተገለጸ። 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለተከላ ተዘጋጅቷል። More stories በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላከው አጣሪ ኮሚቴ በፈተና አስተራረም ዙሪያ የደረሰበትን ሂደት ይፋ አደረገ።April 14, 2022 ቴድሮስ አድሃኖም “የአማራ ክልል አሳሰበኝ” አሉAugust 7,… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። መረጃው ቀድሞውንም ዜናው “ሴራ” ነው በሚል አስተያየት ከሰጡ ወገኖች ጋር የሚስማማ ሆኗል። ቀሲስ በላይ መኮንን አፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢው ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ነገሩ ሲነቃ ከተሰወሩ ግለሰቦች ጋር ተገኝተው በሃሰተኛ ሰነድ 6.5… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን ስጋት ላይ ጥሎት አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንዲወስድ ያስገደደው? ከሆነም ህብረቱ ይህን አቋሙን ለምን በይፋ ከማስታወቅ ይታቀባል? ነገሩ በዚህ ደረጃ አሳሳቢ ከሆነ ቢያንስ ሁለት መስመር መግለጫ እንዴት ማውጣት ተሳነው …. ብዙ መወያያ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች